አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ 53 ወለል አስመረቀ

Feb13,2022
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ 53 ወለል አስመረቀየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለ 53 ወለል አስመረቀ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ባለ 53 ወለል እና 209 ነጥብ 15 ሜትር ከመሬት በላይ ከፍታ እና 65 ሺህ ስኩየር ሜትር ስፋት ያለው ህንጻ ዛረ አስመረቀ።

ባንኩ ያስመረቀው ህንጻ በውስጡ እስከ 1 ሺህ 500 መኪና ማቆም የሚችል ዘመናዊ ፓርኪንግ፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ ሙዚየም፣ ሲኒማ ቤት እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ይዟል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላለፉት 80 ዓመታት ለደንበኞች ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ሲሰጥ ቆይቷል። በተለይም በፋይናንስ እና በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እንዲሁም በወጪ፣ ገቢ እና በአገር ውስጥ ንግድ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ ሲያበረክት እንደቆየም ይታወቃል።



ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ የፋይናንሰ ዋርካ ነው ብለዋል።
ለዚህም ደግሞ ባንኩ በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ባንኮች ካላቸው ተቀማጭ ሃብት ከ52 በመቶ በላይ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል፡፡ ለባንኩ ህንጻ ግንባታ 303.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጏል። ህንጻው 4ሺህ ሰራተኞችን ማስተናገድ ይችላል።

በተጨማሪ ባንኩ በአገሪቱ በዘርፉ ካለው አጠቃላይ ሃብት ውስጥ ከ62 በመቶ በላይ የሚሆነውን መያዙም ባንኩን የፋይናንስ ዋርካ ያሰኘዋል ነው ያሉት። አሁን ላይ ከአንድ ትሪሊየን ብር በላይ ሃብት ያለው ባንክ መሆኑም ሌላኛው የዋርካነቱ መገለጫ መሆኑን አንስተዋል።



በሌላ በኩል ባንኩ ኢትዮጵያ ተቋማትን በመገንባት ለትውልድ ማሸጋገር እንደምትችል ህያው ምስክር መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ታሪክ የፋይናንስ መዝገበ ቃላት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ባንኩ የማያልቅ እውቀት ባለቤት መሆኑንም መስክረዋል። “የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዩኒቨርስቲ” ሲሉ ባንኩ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን በማፍራት ረገድ ያበረከተውን አስተዋጽኦ ገልጸዋል፡፡

Related Post