አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ

Feb19,2024
የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያየካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ

‘’የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016’’ ከጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራ ላይ ውሏል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን “የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ አሰጣጥ እና ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 980/2016” በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር መመዝገቡን እና በስራ ላይ መዋሉን በደስታ ይገልፃል። ይህ መመሪያ ባለሥልጣኑ ከሚያወጣቸው መመሪያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውን የካፒታል ገበያ ተግባራት፣ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲሁም ፈቃድ የወሰዱ አገልግሎት ሰጪዎች የሚኖርባቸውን ኃላፊነት እና ግዴታዎች በመደንገግ በካፒታል ገበያ ውስጥ ላሉ አገልግሎት ሰጪዎች አጠቃላይ የህግ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ታዬ እንደገለጹት “ይህ መመሪያ በሃገራችን የካፒታል ገበያን ለማስጀመር ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን ገበያው ተዓማኒ እና ፍትሐዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚረዳ እና የኢንቨስተሮችን ጥበቃ የሚያጎለብት የሕግ ማዕቀፍ ይሆናል።”

በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ 15 የተለያዩ የፈቃድ ዓይነቶች ይኖራሉ። እነዚህ ፈቃዶች የሚሰጡት በመመሪያው ላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ለሚያሟሉ አመልካቾች ሲሆን ባለሥልጣኑ እነዚህን አገልግሎት ሰጪዎች የሚቆጣጠር ይሆናል።

ባለሥልጣኑ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ለማስጀመር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል።

Related Post