አርእስተ ዜና
Tue. Apr 30th, 2024

ከ235 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

Apr13,2024
ከ235 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙከ235 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከመጋቢት 29 ቀን እስከ ሚያዚያ 3 2016 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 169 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 66 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 235 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣የመኪና መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ የቁም እንስሳት፣የጦር መሳሪያ እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ቃሊቲ፣ ጅግጅጋ እና ድሬድዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 100 ሚሊዮን፣ 46 ሚሊዮን እና 31 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን ኮንትሮባንዱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 13 ተጠርጣሪዎች እና ስድስት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Related Post