አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ የተደረጉ ዕቃዎች

Dec24,2023
ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ የተደረጉ ዕቃዎችከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ የተደረጉ ዕቃዎች

ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ዕቃዎች፣ የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግርን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል እንዲሁም ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ ይጣላል፡፡

ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች
ከኤክሳይዝ ታክስ ነጻ ከተደረጉ እቃዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-
1. ከተሽከርካሪ በስተቀር ወደሀገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እቃዎች፣
2. በመንግስት ጥሪ መሰረት በአደጋ የተጐዱ ሰዎችን ለመርጃ እንዲውሉ ወደሀገር የሚገቡ ዕቃዎች፣
3. ወደሀገር የሚገቡ መንገደኞች ይዘዋቸው የሚመጡ አግባብ ባለው ሕግ የተፈቀዱ ዕቃዎች፣ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ዕቃዎች፣
4. ሚኒስትሩ በሚፈርመው ወይም በሚያፀድቀው ስምምነት የተፈቀዱ በዕርዳታ ለሚካሄዱ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ ወደሀገር የሚገቡ ወይም ከሀገር ውስጥ የሚገዙ ዕቃዎች፣

5. የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር/የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ወደሀገር የሚያስገቧቸው ወይም ከሀገር ውስጥ የሚገዙዋቸው በሚኒስትሩ በሚወጣ መመሪያ የተፈቀዱ ዕቃዎች፣
6. የአካል ጉዳተኞች ወደሀገር እንዲያስገቡት የተፈቀደ ለአካል ጉዳተኞች እንዲያገለግል ሆኖ የተሠራ አንድ የግል ልዩ ተሽከርካሪ፣
7. አውሮፕላን በዓለም ዐቀፍ ትራፊክ እንቅስቃሴ ውስጥ ባለበት ጊዜ በጉዞ ወቅት የሚጠቀሙባቸው በነፃ የሚሰጡ ዕቃዎች፣
8. በዲፕሎማቶች መብትና ጥቅም ደንብ የተፈቀዱ ዕቃዎች፣
9. በአደጋ ወይም በሌላ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የጠፉ ወይም የተበላሹ ዕቃዎች፣

10. በኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብ መሠረት ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ኢንቬስተሮች ወደሀገር የሚያስገቧቸው የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው ዕቃዎች፣
11. ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ የተደረጉ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ነፃ የተደረጉ ዕቃዎች፣
12. ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የመሆን መብት ላላቸው አካላት የሚሸጡ ዕቃዎች፣
13. ለሕክምና አገልግሎት እንዲውል ለሰው በመጠጥነት አገልግሎት ሊሰጥ በማይችልበት አኳኋን የተመረተ አልኮል፡፡

ምንጭ: የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post