አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በድሬዳዋ ከተማ ተጀመረ

Jan28,2024
የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በድሬዳዋ ከተማ ተጀመረየ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በድሬዳዋ ከተማ ተጀመረ

በአንዋር ሁሴን – ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ሳምንት ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ጂግጂጋ ከተሞች ለአገልግሎት ያበቃውን የ5ኛ ትውልድ የሞባይል አገልግሎት በምስራቅ ሪጂን በድሬዳዋ ከተማ በመዘርጋት በይፋ ማስጀመሩን ገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት በድሬዳዋ ከተማ ባሉት አካባቢዎች በሰባት ቦታዎች ማለትም በሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ አሸዋ ገበያ፣ ከዚራ ቴሌ፣ ቢ-ካፒታል ሆቴል፣ በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በተስፋ ሆቴል እና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ አገልግሎቱን አስጀምሯል፡፡

የ5ጂ አገልግሎት ስራ ላይ መዋል የቢዝነስ ደንበኞቻችን ምርታማነታቸውን እና የአሠራር ቅልጥፍናቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ፣ በዘመናዊ መተግበሪያዎች አማካኝነት አዳዲስ ገቢዎችን እንዲያገኙ ለማስቻል፣ የቢዝነስ ትንታኔን በቀላሉ በማግኘት ከንግድ ለውጦች ጋር በፍጥነት እንዲላመዱ እገዛ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪም ተለዋዋጭ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለተልዕኮ-ወሳኝ የሆነ ፈጣን የዳታ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ የማሕበረሰባችንን ሕይወት በማቅለል በኩልም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነው፡፡

የ5ጂ የሞባይል አገልግሎት ለዘመናዊ ቤት (Smart home) ፣ ለስማርት የጤና አገልግሎት እና የሆስፒታል አስተዳደር፣ ለስማርት ግብርና፣ ትምህርት፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ለስማርት ኤርፖርትና የጉዞ አገልግሎት፣ ለስማርት ትራንስፖርት፣ ለብሮድካስቲንግና ለመዝናኛ እንዲሁም በክላውድ ላይ ለተመሰረቱ የ5ጂ ጌሞች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው የዘመናችን የመጨረሻው ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊ.ባ በሰከንድ (Gbs) የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን እጅግ በላቀ ሁኔታ በመቀነስ (Ultra-low latency) ወደ 1ሚሊ በሰከንድ የሚያደርስ ነው፡፡ በተጨማሪም በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር ውስጥ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ በርካታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እርስ በርሳቸው ለማገናኘት የሚያስችል ዓለማችን የደረሰበት ዘመናዊ የገመድ አልባ ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

በተለይም ወሳኝ ተልዕኮ ላላቸው (Mission Critical) እና በተመሳሳይ ወቅት (real time) መከናወን የሚፈልጉ አገልግሎቶችን ለአብነትም የማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ግብርና፣ ህክምና፣ ለመሳሰሉ ኢንዱስትሪዎች እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው፡፡ እንደ ሹፌር-አልባ ተሽከርካሪዎች (self-driving vehicles) ፣ Internet of Things የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎችም በተግባር እውን እንዲሆኑ የሚያስችል አስተማማኝ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ኩባንያችን ለክቡራን ደንበኞቹ የ5ጂ ያልተገደበ ዳታ፣ የመደበኛ የመኖሪያ ቤት ዳታ እንዲሁም የተለያዩ የ5ጂ ጥቅል አማራጮችን ያቀረበ ሲሆን፣ ደንበኞች የ5ጂ አገልግሎትን መጠቀም በሚያስችሉ መሳሪያዎችና ቀፎዎች አማካይነት አገልግሎቱን የሚችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን፡፡

Related Post