አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የፈፀመችው የባህር በር ስምምነት ላይ ዉይይት ተካሄደ

Jan4,2024
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የፈፀመችው የባህር በር ስምምነት ላይ ዉይይት ተካሄደኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የፈፀመችው የባህር በር ስምምነት ላይ ዉይይት ተካሄደ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ከአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን ኢትዮጵያ የባህር በር ለመጋራት ከሶማሌላንድ ጋር የፈፀመችውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ ውይይት ተካሄደ።

በውይይት መርሃግብሩ የብሪክስ አባል ሀገር መሆናችን በተረጋገጠ ማግስት ከሶማሌ ላንድ ጋር የባህር በር ለመጋራት የመግባቢያ ስምምነት መፈፀም መቻሉ ለአምራች አንዱስትሪው ፋይዳው የላቀ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት ጥራታቸውንና የማምረት አቅማቸውን በማሻሻል ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ የኢኮኖሚ አበርክቶ ከፍ እንዲል በማድረግ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የብሪክስ አባል ሀገር መሆን መቻላችን ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሚኖረንን ሁሉ አቀፍ ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር እያካሄድን ላለው የኢኮኖሚ ዕድገት መሳካት ድርሻው የላቀ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የራሷ በርካታ ወደቦች ባለቤት የነበረች ሀገር መሆኗን በመጥቀስ ሁሉም የአለም ሀገራት ወደብን በሰላማዊ መንገድ ሁለቱንም ወገን የጋራ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የሚከናዎን ነባራዊ እውነታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከሁሉም ጎረቤት ሀራት ጋር አስፈላጊውን ሁሉ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብት ሰላማዊ በሆነ መንገድ በጋራ መርህ ላይ በመመስረት መጠቀም ይኖርብናል።

ስምምነቱ ለ50 ዓመታት የሚቆይ ስምምነት ነው ያሉት አቶ መላኩ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይላችንን ለጎረቤቶቻችን እያጋራን እንደሆነ ሁሉ የወደብ መጋራት ስምምነቱም በተመሣሣይነት ሁኔታ ሊታይ እንደሚገባው ገልፀው ጎረቤቶቻችን ችግር በገጠማቸው ጊዜ ሁሉ በምንችለው ከጎናቸው ሆነን ችግራቸውን እየተጋራን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ስምምነቱ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ አቶ መላኩ ለማህበራዊ ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች መስተካከል ቁልፉ መፍትሄ ለሁሉም የሚተርፍ ሀብት መፍጠር መሆኑን በመጠቆም ከሁሉ በላይ ተቀዳሚው ስራችን አምራች ኢንዱስትሪው ሀገራዊ የኢኮኖሚ ድርሻ ከፍ እንዲል ሊሆን ይገባል ብለዋል ።

የዕድገትና ተወዳዳነት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው ሁሉም ሀገር ለብሔራዊ ጥቅሙ የቅድሚያ ቅድሚ ሰጥቶ እንደሚሰራ በመግለፅ ሁላችንም ስለ ኢትዮጵያ ሀገራችን አዎንታዊ አስተሳሰብን በመገንባት ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት መረጋገጥ፣ ሰላም መስፈንና ዲፕሎማሲያዊ ድል ልንረባረብ ይገባል።

Related Post