አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

የመንግሥት ተቋማት የሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

Feb12,2022
የመንግሥት ተቋማት የሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደየመንግሥት ተቋማት የሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የመንግሥት ተቋማት ሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ላይ በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ በዚህ ሳምንት ውይይት አካሄዷል፡፡ የዕትሂኦፒአ

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያካሄደው ውይይት የመንግሥት ተቋማት ዕቅድ ጥራት ያለው፣ ውጤታማ እና የጋራ እንዲሆን ያለመ ነው፡፡ ይህ ዕቅድ በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የ100 ቀናት ዕቅድ የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መታረም ያለባቸው ጉዳዮች እንዲለዩ እንዲሁም እንዲጨመር አጽንዖት የሰጡባቸውን ጉዳዮች ለማካተት የታቀደ መሆኑ ተነግሯል።



መድረኩን የከፈቱት የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ፣ የዕቅድ አፈፃፀም የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ እንደዚህ ዐይነት ውይይት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰው፣ የልማት ዕቅዱ የአፈፃፀም ስርዓቱን በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በቀደመው ዕቅድ ላይ ሪፖርቱን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ያለማቅረብ፣ የመረጃ መፋለሶች መኖር፣ ሪፖርቱን በተዘጋጀው DMRS ላይ ያለ መጫን፣ የአመልካች እና ፕሮጄክቶችን ሪፖርት መቀላቀል እንደ ድክመት ስለተጠቀሰ፣ እነዚህ እና ሌሎች ድክመቶች ተለይተው በታዩ ጥንካሬዎች ላይ በማተኮር መስተካከል እንደሚርባቸር ጠቁመዋል።



ይህ የሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ከአንድ ዓመት ዕቅዱ ውስጥ የተወሰደ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታዋ፣ ቀጣዩን የሶስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ ዘመናዊ በሆነ መንገድ፣ ከጅማሮው እስከ አፈፃፀሙ የሁሉንም ትብብር የሚፈልግ፣ በተለይ ደግሞ የተጠያቂነትን ጉዳይ የሚያጠናክር መሆኑን አመልክተዋል። በዚህ የውይይት መድረክ ላይ ከ22ቱም የፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለሞያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Related Post