አርእስተ ዜና
Sat. May 4th, 2024

ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ

Feb15,2022
ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሃገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ።

ምክር ቤቱ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የወሰነው። ይህን ውሳኔ ተከትሎ÷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡



በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ አሰጣጥ ስርአት እንዲያጠናቅቁም ተወስኗል። በትላንትናው እለት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ በአራት አጀንዳዎች ላይ ከተወያየ በኋላ አጀንዳዎቹ ዛረ በሚካሄደው የም/ቤቱ አስቸኳይ ጉባዔ እንዲቀርብ መወሰኑ ይታወቃል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጨምሮ፣ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅን፣ የግል ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ የውሳኔ ሃሳብን ነው አማካሪ ኮሚቴው በአጀንዳነት የተወያየባቸው።

አማካሪ ኮሚቴው በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጀንዳ አስመልክቶ በስፋት የተወያየ ሲሆን ፣ የአዋጁ መነሳት በአዋጁ መደንገግ አጋጥሞ የነበረውን ምጣኔ ሃብታዊ ፣ ዲፕሎማሲያዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ ለመፍታት ሚናው የጎላ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ እና የአማካሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ አብራርተዋል።

አዋጁ እንዲነሳ ሲታሰብ የሀገሪቷን የፀጥታ ስጋት ባገናዘበ መልኩ መታየቱንና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሊፈቱ እንደሚችሉ ስለታመነበት መሆኑን አቶ ታገሰ ገልፀዋል።

የአማካሪ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው፣ አሸባሪዎቹ ሕወኅት እና ሸኔ የፀጥታ ስጋት እንደሆኑ ናቸው ፣ አዋጁ ከተነሳ ችግሩን ለመፍታት ምን ታስቧል ሲሉ ጠይቀዋል።
የፀጥታ ስጋት ባለባቸው የአማራ ፣ አፋር ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ጋንቤላና ወለጋ አካባቢዎች መንግስት የማስተካከያ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ታገሰ አብራርተዋል።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክተው ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ እና ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እንደሚሰጡ አፈ-ጉባዔው ጠቁመዋል ።



የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው፣ የሀገሪቷ የፀጥታ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን ጠቅሰው፣ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች የተለየ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ Amharic

መንግሥት ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ Amharic

Related Post