አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

በቡድን የተደራጁ ወንጀለኞችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያዘ

Oct5,2022
በቡድን የተደራጁ ወንጀለኞችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያዘበቡድን የተደራጁ ወንጀለኞችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ያዘ

በቡድን በመደራጀት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ንብረት የሆነ ከ7መቶ ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው የኤሌክትሪክ ገመድ በመስረቅ በተሽከርካሪ ጭነው ለማምለጥ የሞከሩ 8 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው አጃምባ ኮንዶሚኒየም ሳይት ውስጥ ነው፡፡ ግለሰቦቹ በለሊቱ ክፍለ ጊዜ ጭለማን ተገን በማድረግና በቡድን ተደራጅተው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ንብረት የሆነ 7 መቶ 28 ሺህ ብር የዋጋ ግምት ያለውን 616 ጥቅል የኤሌክትሪክ ገመድ የመጋዘኑን በር ሰብረው ከሰረቁ በኋላ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ-3-10402 ኦሮ በሆነ አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ጭነው ለማምለጥ ሞክረዋል።

በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ከመስሪያ ቤቱ የጥበቃ ሰራተኞች እና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት የተሰረቀውን ንብረት ጨምሮ 8 ግለሰቦች ከእነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ምንጭ: የአዲስ አበባ ፖሊስ

Related Post