አርእስተ ዜና
Tue. Apr 30th, 2024

በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ማራይን የተባለ ማዕድን ተያዘ

Dec5,2022
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ማራይን የተባለ ማዕድን ተያዘበሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ማራይን የተባለ ማዕድን ተያዘ

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ትናንት በድሬዳዋ ከተማ ባደረገው ክትትል በተለምዶ ሶስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ እና 4 ነጥብ 1 ኪ.ግ የሚመዝን ‘አኳ ማራይን’ የተባለ ማዕድን በቁጥጥር ስር አውሏል።

ሕገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ማዕድኑን ወደ ውጭ ሀገር ለማስወጣት እና ለመሸጥ በዝግጅት ላይ እንዳሉ በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም በብሄራዊ መረጃ ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

በሕግ ማስከበር ስራው የሀገር ሐብቱን ሲያዘዋውሩ የተገኙ አራት ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ የተያዘው ማዕድንም በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ቀጣይ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በሕግ ማስከበር ዘመቻው ተሳትፎ ላደረጉ የድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች እንዲሁም ለፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋና አቅርቧል።

ምንጭ: የጉምሩክ ኮሚሽን

Related Post