አርእስተ ዜና
Sun. Apr 28th, 2024

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከመንግስት ጣልቃገብነት ነጻ ወጣ

Aug5,2023
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከመንግስት ጣልቃገብነት ነጻ ወጣየአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከመንግስት ጣልቃገብነት ነጻ ወጣ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት አርብ ባካሄደው 23ኛው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ይህም ዩኒቨርሲቲዉን ከመንግስት ጣልቃገብነት ነጻ ያወጣዋል ተብሎ ታመናል። ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የተንቀሳቃሽ ምስል ዘናዎች
https://youtu.be/EnXX1O6C6Os

Related Post