አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመከላከል አቅጣጫ ተቀመጠ

Aug8,2023
ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመከላከል አቅጣጫ ተቀመጠህገወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመከላከል አቅጣጫ ተቀመጠ

ህገወጥ የሰዎችን ዝውውር በተለያዩ ስልቶች መከላከል ብሎም የዝውውር ሰንሰለቱን በተቀናጀ ህግ የማስከበር ስራ መበጣጠስ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን የብሔራዊ ፍልሰት ትብብር ጥምረት አስታውቋል፡፡

ጥምረቱ በአዳማ ባደረገው ግምገማ የፍልስተኞችን መረጃ በአግባቡ መያዝ፣ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ከሚሄዱባቸው ሀገራት ጋር መፈራረም እና የጥምረቱን ባለድርሻ አካላት ማጠናከር የ2016 ሌላው የትኩረት ጉዳዮቹ ናቸው፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚደገፈው የብሄራዊ ፍልሰት ትብብር ጥምረት የተቋቋመው ፍልሰትን በአግባቡ ለመምራት እና ለማስተዳድር ነው፡፡

በኢጋድ የፍልሰት አስተዳደር አስተባባሪ ሙጂብ ጀማል ድርጅታቸው ጥምረቱን በመደገፍ ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ የያዘችውን እቅድ እንድታሳካ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በአደማ በተካሄደው የጥምረቱ ግምገማ ከውጭ የሚመለሱ ተጎጂዎችን ለመደገፍ ፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ በድንበር አካባቢ ለሚኖር ፍልስት የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ እና መደበኛውን ፍልሰት በተቀመጠለት ህግ መሰረት ለመደገፍ አንዲሁም ኢመደበኛውን ፍልሰት ለመከላከል የክልልና የፌደራል ተቋማት በትኩረት ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

የተንቀሳቃሽ ምስል መረጃዎች
https://youtu.be/vr0dfqIrsro

Related Post