አርእስተ ዜና
Fri. May 17th, 2024

የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት አሰጣጥን በተመለከተ

Apr4,2022
የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት አሰጣጥን በተመለከተ
የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት አሰጣጥን በተመለከተ

በጉምሩክ አዋጅ 1160/2011 መሰረት

1. በገቢና ወጪ እቃዎች ላይ የቀረጥ ነጻ መብት የሚሰጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ብቻ ይሆናል
2. ከዲፕሎማሲ ግንኙነት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ በፈረመችባቸው እና ተቀብላ ባፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች መሰረት የሚሰጡ የቀረጥና ታክስ ነጻ መብቶች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እየተረጋገጠ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

3. የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት እንዲፈቅዱ በሕግ ለተለየዩ የመንግስት አካላት የተሰጠው ስልጣን ለገንዘብ ሚኒስቴር ተላልፏል፡፡
4. ማንኛውም የመንግስት አካል በሚዋዋለው የፕሮጀክት ስምምነት መሰረት የሚፈቀድ የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ተፈጻሚ የሚሆነው በገንዘብ ሚኒስቴር ሲጸድቅ ብቻ ይሆናል፡፡

5. የጉምሩክ ኮሚሽን ከቀረጥና ታክስ ነጻ ሆነው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ወይም ከአገር የሚወጡ እቃዎች ለታለመላቸው ዓላማ ስለመዋላቸው መረጃ ይይዛል፤ ይከታተላል፤ እርምጃ ይወስዳል፡፡

6. የቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ስለሚፈቀድበት ሁኔታ እና ስለአፈጻጸሙ ሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡

(ምንጭ-የገቢዎች ሚኒስቴር)

Related Post