አርእስተ ዜና
Tue. Apr 30th, 2024

ከ171 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

Apr3,2022
ከ171 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙከ171 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

ባሳለፍነው ሳምንት 171 ሚሊዮን 421 ሺህ ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 166 ሚሊዮን 194 ሺህ ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 5 ሚሊዮን 226 ሺህ ብር የሚያወጡ የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ሞያሌ እና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 28 ነጥብ 2 ሚሊዮን፣ 23 ነጥብ 6 ሚሊዮን እና 22 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ ስምንት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

4 Comments

Related Post