አርእስተ ዜና
Sat. May 4th, 2024

የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ በ7 ወራት 7.42 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

Feb18,2022
የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ በ7 ወራት 7.42 ቢሊየን ብር ሰበሰበየምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ በ7 ወራት 7.42 ቢሊየን ብር ሰበሰበ

በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2014 በጀት ዓመት በ7 ወራት ውስጥ 5.97 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 7.42 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ እንደገለጸው ከሆነ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የታክስ ህግ እውቀት እንዲኖራቸውና የህግ ተገዥነት ደረጃቸውን ለማሳደግ እንዲቻል ከግብር ከፋዮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ 7 ወር እቅድ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ሪፖርቱን ያቀረቡት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቃለህይወት መኮንን ገልፀዋል፡፡



በመድረኩ በ2013 በጀት አመት ሊካሄድ የነበረውና በኮቪድ 19 እና በጦርነቱ ምክንያት ሳካሄድ የቆየው የግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት መርሃ ግብርም ተካሂዶ የተሻለ የህግ ተገዥነት ላሳዩ 20 ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ አፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ ለሽልማት የበቃችሁ ታማኝ ግብር ከፋዮች እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ ግብርን በታማኝነት መክፈል ከልመናና ከተመፅዋችነት የተላቀቀች ሃገር የመገንባት ራእያችንን ማሳካት ማለት ነው በማለት ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም የታክስ ህግ ተገዥነትን ለማስፈን የግብር ከፋዩን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ግብር የመክፈል ባህል ለማሳደግ የግንዛቤና የንቅናቄ ስራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡



በመድረኩ ተጋባዥ የነበሩት እና የታክስ አምባሳደር የሆኑት መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ለተሸላሚ ግብር ከፋዮች እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ባስላለፉበት ወቅት ያለችን አንድ ሀገር በመሆኗ የሚገባንን ወስደን ለሀገር የሚገባውን መስጠት ልማድ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
በውይይቱ ግብር ከፋዮች ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከባንክ የሲስተም መቆራረጥ ጋር በተያያዘ የክፍያ ችግር እንዲሁም ሌሎች ያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

Related Post