አርእስተ ዜና
Wed. May 1st, 2024

ኢትዮጵያ ቅድመ ጭነት ምርመራ ያልተደረገላችውን የሶላር ምርቶች እንዳይገቡ አገደች

Feb18,2022
ኢትዮጵያ ቅድመ ጭነት ምርመራ ያልተደረገላችውን የሶላር ምርቶች እንዳይገቡ አገደችኢትዮጵያ ቅድመ ጭነት ምርመራ ያልተደረገላችውን የሶላር ምርቶች እንዳይገቡ አገደች

ኢትዮጵያ መንግስት ቅድመ ጭነት ምርመራ (ኢንስፔክሽን) ያልተደረገላችውን የሶላር ምርቶች እንዳይገቡ ማገዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ጋር በመተባባር አለም አቀፍ ጨረታ በማውጣት ጨረታውን ካሸነፉ Bureau Veritas እና Cotecna ከተሰኙ ሁለት አለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት በመፈራረም ከጥር 17/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ጭነት ኢንስፔክሽን ፕሮግራሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ መልክ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡



ማንኛውም የሶላር ቴክኖሎጂና ተያያዥ መለዋወጫ ምርቶችን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባ አስመጪ ድርጅት ከሁለቱ አሸናፊ ኩባንያዎች የአንዱን የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የማቅረብ ግዴታ እንዳለበት የገለጹት በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪና ገቢ እቃዎች ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ እያሱ ስምኦን ያለ ጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚመጡ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ፍቃድ የማይሰጥና ወደ መጡበት ሀገራት እንዲመለሱ የሚደረግ መሆኑ ታውቆ ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የምርቶቹን ጥራት በላብራቶሪ ለመፈተሽ ረዘም ያለ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ እና በሀገር ውስጥ በቂ የላብራቶሪ የመፈተሽ አቅም የተገነባ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ምርቶቹ ከሚላኩባቸው ሀገራት አለም ዓቀፍ ዕውቅና ባላቸው የሦስተኛ ወገን የጥራት አረጋጋጭ ኩባንያዎች ጥራታቸው ተረጋግጦ የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይዘው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን አሰራር መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡



ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የጥራት ቁጥጥር ከሚደረግባቸው ምርቶች መካከል ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ በአዲስ መልክ የቅድመ ጭነት ኢንስፔክሽን ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረጉ ገልጿል፡፡

Related Post