አርእስተ ዜና
Fri. Apr 26th, 2024

አዘርባጃን፡ አፍሪካ ማዳበሪያ እንድታመርት ማገዝ ትፈልጋለች ተባለ

Aug11,2020
አዘርባጃን፡ አፍሪካ ማዳበሪያ እንድታመርት ማገዝ ትፈልጋለች ተባለአዘርባጃን፡ አፍሪካ ማዳበሪያ እንድታመርት ማገዝ ትፈልጋለች ተባለ

የአዘርባጃን መንግስትና ባለሃብቶች የአፍሪካ ሀገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ በማዳበሪ ምርት እራሳቸዉን እንዲችሉ ማገዝ እንደሚፈልጉ በኢትዮጵያ የአዘርባጃን አምባሳደር ገለፁ፡፡

በኢትዮጵያ፤በኬኒያና በጅቡቲ የአዘርባጃን አምባሳደር የሆኑት ኢልማን አብዱላየቭ በተለይ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት ከሆነ ሀገራቸዉ በዙ የአዉሮፓ ሀገራት በማዳበሪያ ምርት እራሳቸዉ እንዲችሉ የረዳች ሲሆን በአፍሪካ ሀገራትም በተመሳሳይ በእርሻ ማዳበሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እንዲገነቡ ማገዝ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በሃገሪቱ የማዳበሪያ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በጣም እያደገ ሲሆን ሃገራቸዉ ብዙ የአዉሮፓ ሃገራትን በማዳበሪያ ምርት ሙሉ በሙሉ እራሳቸዉን እንዲችሉ እንዲሁም የማደበሪያ ማምረቻ ኢንዱስትሪ እንዲኖራቸዉ አግዘናል ያሉት አምባሳደሩ አክለዉም ከሌላዉ አለም በተሻለ መልኩ በአፍሪካ የማዳበሪ ምርት ለማምረት የተመቸ ነዉ ለዚህም ሀገራችን በአፍሪካ በማደበሪያ ምርት እራሷን እንድችል እንደምትፈልግ ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ ማዳበሪያ አምራች ኢንዱስትሪን ለማሳደግ የአዘርባጋን ባለሃብቶች በአፍሪካ የምግብና የኬሚካል ኢንድስትሪ ዘርፎች ላይ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡ሃፈራቸዉ የምትገኝበት ስትራቲጂካል ቦታ ከ300 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለሚኖርበት ቀጠናዉ ለገበያ ተመራጭ እንበሚያደርጋት ተናግረዋል፡፡

ሌሎች ሀገራት እሴት ያልተጨመረበት የኢትዮጵያን ቡና ገዝተዉ ሀገራቸዉ እንደሚያቀነባብሩት የተናገሩት አምባሳደር ኢልማን አብዱላየቭ ሃገራቸዉ ግን የተቀነባበሩና የተሸገ ቡና ወደ ሀገራቸዉ እንደሚያስገቡ ገልፀዋል፡፡ከዚም በተጨማሪ አኮር የተባለ በአዉሮፓ የታወቀ የአዘርባጃን የኮንስርትራክሽን ኩባንያ የዚትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ በመሳተፍ ላይ መሆኑን አምባሳደሩ ለኒዉ ቢዝነስ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡
[embedyt] https://www.youtube.com/watch?v=OkS6KgEn4vQ[/embedyt]

Related Post