አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

በየካቲት 46 ሺህ 603 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ማግኘታቸው ተገለፀ

Mar21,2022
በየካቲት 46 ሺህ 603 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ማግኘታቸው ተገለፀበየካቲት 46 ሺህ 603 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ማግኘታቸው ተገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፀጥታ ችግር ያለባቸው አካባቢዎችን ሳይጨምር በየካቲት ወር 2014 ዓ.ም ለ46 ሺህ 603 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጷል፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት የካቲት ወር አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር በ15 ሺህ 768 ብልጫ አሳይቷል ተብሏል፡፡ ይህ የተባለው ዛሬ የተቋሙ ከፍተኛ ሥራ አመራር የ2014 በጀት ዓመት የካቲት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በበይነ መረብ አማካኘነት በተወያየበት ወቅት ነው፡፡



በውይይቱም 19 አዳዲስ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ተገልጿል፡፡ በየካቲት ወር በአጠቃላይ 1 ሺህ 229 ለሚሆኑ ዜጎች በፕሮጀክትና በመደበኛ የስራ ዕድል እንዲፈጥር መደረጉንም ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ ሁሉም የድህረ-ክፍያ ደንበኞቹ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ ሂሳብ ከተቋሙ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በተጨማሪ ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌ ብር፣ በCBE ብር፣ በኢንተርኔትና በሞባይል ባንኪንግ እንዲከፍሉ ማስቻሉ አስራርን ቀልጣፋ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተብሏል፡፡

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሉ 5 የክፍያ አማራጮች አማካኝነት በመጠቀም የሚከናወነው ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ ከአጠቃላይ የክፍያ መጠኑ 27 በመቶ መደረሱንም ተመላክቷል፡፡



ይህ ቁጥር አሁንም አነሰተኛ በመሆኑ አሁንም ደንበኞች በተዘረጉ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ተጠቅመው ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳባቸውን በቀላሉና ባሉበት ቦታ እንዲከፍሉ ተጠይቋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ችግር፣ በአንዳንድ ክልሎች የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰው ውድመት፣ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከውጭ የሚገቡ ግብዓቶች አቅርቦት መዘግየት በወሩ የተስተዋሉ ዋና ዋና ማነቆዎች መሆኑን በቀረበው ሪፖርት ተጠቁሟል፡፡
በበይነ መረብ አማካኘነት የተካሄድው ይህ ውይይት፤ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ ሁሉም የከፍተኛ አመራር አባላት ተሳትፈውበታል፡፡

Related Post