አርእስተ ዜና
Sat. Apr 20th, 2024

ኢትዮጵያና እና አሜሪካን በንግዱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

Mar22,2022
ኢትዮጵያና እና አሜሪካን በንግዱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙኢትዮጵያና እና አሜሪካን በንግዱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሃመድ በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሲ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን አሊ ጄ ናዲርን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኢታው ሃላፊውን በቢሯቸው ተቀብለው ባነጋሩበት ወቅት ሁለቱ እህትማማች ሃገራት የቆየ ታሪካዊ ወዳጅነት እንዳላቸውና ይህም ወዳጅነት የጋራ ተጠቃሚነትን ባማከለ መልኩ እንደሆነና የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን የቆየ ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ አበክሮ ይሰራል ብለዋል፡፡



በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ እየተከሰተ ያለውን የዋጋ ንረት ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን እና ይህም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሲ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑትን አሊ ጄ ናዲርን አሜሪካ ለአፍሪካ ሃገራት ከሰጠችው ዕድል አንዱ አጎዋ መሆኑን ተናግረው የዚህ ዕድል መሰረዝ ሃገሪቱን እንደሚጎዳት የአሜሪካ መንግስት ይረዳል ያሉት ሃላፊው የአሜሪካ መንግስትም ጉዳዩን በትልቅ አጀንዳነት ይዞ እየተንቀሳቀስ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

አሊ ጄ ናዲርን በበኩላቸው የሁለቱ ሃገራት ግንኑኘት ታሪካዊ እና በምንም መልኩ ሊሸረሸር እንደማይችልና ይህም የቆየ ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማደግ እንደሚገባው ገልጸው ኢትዮጵያና እና አሜሪካን በንግዱ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡

Related Post