አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግብር ገቢ ተላለፈ

Sep17,2022
ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግብር ገቢ ተላለፈከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግብር ገቢ ተላለፈ

ከ41 ቢሊዮን ብር በላይ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የግብር ገቢ መተላለፉ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የፌዴራል፣ የክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች የገቢ ዘርፍ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ የገቢዎች ሚኒስቴር የፌደራል እና የክልል መንግስታትን የጋራ ገቢን እና በውክልና የሚሰበሰቡ ታክሶችን ሰብስቦ ለክልሎች የሚያስተላልፍ መሆኑን አንስተው በ2014 በጀት ዓመት 34.69 ቢሊዮን የጋራ ገቢ እና 6.325 ቢሊዮን የውክልና ታክሶችን በመሰብሰብ በጥቅሉ 41.02 ቢሊዮን ለክልሎች ማስተላለፉን አንስተዋል::

ሚኒስትሯ አክለውም በ2014 በጀት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ 497.45 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 481.71 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ መቻሉን ገልጸው በ2015 በጀት ዓመትም በሀገር አቀፍ ደረጃ 646.75 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ እቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

ከ2014 በጀት ዓመት እቅድ ክንውን እና ከ2015 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ በተጨማሪ የታክስ ከፋዮች ትምህርት እና የሞጁላር ስልጠና ምንነት እና ጠቀሜታ ላይ፣ የታክስ ውሳኔ ቅሬታ አፈታት በተመለከተ እና የተገልጋዮች ቻርተር ዝግጅት እና ትግበራ የተመለከተ የልምድ ልውውጥ እና ውይይት በቀጣይ ከመድረኩ የሚጠበቁ የመወያያ ርዕሰ ጉዳዮች መሆናቸውን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post