አርእስተ ዜና
Sat. Apr 27th, 2024

ስለ ንግድ ማጭበርበር ወንጀል መጥቂቱ

Oct21,2023
ስለ ንግድ ማጭበርበር ወንጀል መጥቂቱስለ ንግድ ማጭበርበር ወንጀል መጥቂቱ

ኮንትሮባንድም ሆነ የንግድ ማጭበርበር ሁለቱም ህገ ወጥ ንግድ በሚለው ስር ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በወንጀሉ አፈፃፀም አንዱ ከሌላው ይለያል፡፡

“ማጭበርበር” ማለት እውነት ያልሆነውን ነገር እውነት አስመስሎ ማቅረብ ማለት ሲሆን ሐሰተኛ መግለጫዎችንና ትክክለኛ ያልሆኑ ሰነዶችን ማቅረብና በሂደት በሚኒስቴሩ ዘንድ የሚፈጠረውን ስህተት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ቀረጥና ታክስ ሊከፈልባቸው የሚገባቸውን ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ ሳይከፍል ወይም አሳንሶ በመክፈል ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ወይም ከአገር ለማስወጣት ጥረት ማድረግ የወንጀሉ መገለጫዎች ናቸው፡፡

ይህ የወንጀል ድርጊት በእንግሊዘኛው ህግ ቋንቋ የሚታወቀው “smuggling” በሚለው ቃል ነው፡፡ የዚህ ቃል ተቀራራቢ የአማርኛ ፍቺ “መደበቅ” ማለት ሲሆን በህጋዊ ዕቃ ሽፋን ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸውን ዕቃዎች ህጋዊ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ከተፈፀመባቸው ዕቃዎች ጋር ቀላቅሎ ለማስገባት ወይም ለማስወጣት መሞከር ነው፡፡

ወንጀሉ ከኮንትሮባንድ ወንጀል የሚለየው ትክክለኛ መግለጫ ቀርቦባቸው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሊፈፀምባቸው ከመጡት ዕቃዎች ጋር በመቀላቀል መግለጫ ያልተሰጠባቸውን ወይም ትክክለኛ ያለሆነ መግለጫ የቀረበባቸውን ዕቃዎች ቀረጥና ታክስ ሳይከፍል ወይም አሳንሶ በመክፈል ጉምሩክን አታልሎ ለማለፍ የሚደረግ ጥረት /ሙከራ/ መሆኑ ነው፡፡

የኮንትሮባንድ ወንጀል የሚፈፀመው ጉምሩክ ሳያይና ሳይሰማ ወይም ዕቃውን ለመፈተሽ ምንም ዓይነት ዕድል እንዳይኖረው በማድረግ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የኮንትሮባንድ ዕቃ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ሊፈፀምባቸው ለጉምሩክ ከሚቀርቡ ዕቃዎች ጋር ተቀላቅሎ የሚቀርብ አይደለም፡፡
ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስተር

Related Post