አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ለአስደናቂዋ ታጋይ፣ ለነፈሰባት መሪ – ኦንግ ሳን ሱ ቺ

ለአስደናቂዋ ታጋይ፣ ለነፈሰባት መሪ - ኦንግ ሳን ሱ ቺ
ለአስደናቂዋ ታጋይ፣ ለነፈሰባት መሪ - ኦንግ ሳን ሱ ቺ

አፈር ልሳ ትነሳ ይሆናል፣ የተሻለች መሪ ግን ልትሆን ትችላለች?
ጥሩ ሰው ትሆን ይሆናል (አላውቅም)
ነገር ግን የሃገሯን ወሳኝ ኃይሎች ጠርንፋ
(harness አድርጋ ነበር ማለት የፈለግሁት)
ሚያንማርን የተሻለች ሃገር ማድረግ አልቻለችም፡፡

ምክንያቱም ያንን ማድረግ ሌላ ትልቅ ችሎታ ይጠይቃል
ያ ችሎታ ተቃዋሚ በመሆን ብቻ አይገኝም፡፡
እንደሷው ምሁርም ስለሆኑ አይገኝም፡፡

ለሷን መሰል ሰዎች ደጋፊዎች ተጻፈ፡፡


መሪህን ከረብሻ ውስጥ አትፈልግ፡፡
መሪህን ከተቃውሞ ውስጥ አትፈልግ፡፡
መሪህን ወሬ ከሚያሳምሩ ሰዎች ውስጥ አትፈልግ፡፡
መሪህን ከሚሳደቡ ሰዎች ውስጥ አትፈልግ፡፡
መንግስታት የሚሠሩትን ስህተት እየለቀሙ
ተቃውሞ በመግለጽ ተቃዋሚ መሆን ይቻላል
የለውጥ እና የመሻሻል አቀንቃኝ መሆን ይቻላል፡፡
ችግርን በዘመቻ ሰብስቦ በማውራት
ኃላፊነት ላይ ያሉት ሥራቸውን እንዲሠሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
በየመንደሩ፣ በየብሔሩ እየሄዱ ለድምጽ አልባዎች ድምጽ በመሆን
መሪዎች ትኩረት እንዲሰጡ ማድረግ ይቻላል፡፡
ለማይ ካድራ ሻማ ማብራት
ለመተከል ጥቅር እንባ ፎቶ መለጠፍ
ለትግራይ መሬት ላይ መተኛት ይቻላል፡፡
ይሄ ትግል ሊሆን ይችላል፡፡
ይሄን ያደረገ ሰው ግን ሃገር መምራት ይችላል ማለት አይደለም፡፡
ልትታሰር፣ ልትገረፍ ትችላለህ
በስቃይህ ሁሉ ጽናትህን ልትጠብቅ ትችላለህ፡፡
ሊሠብሩህ ሲሞክሩ በማይሠበረው መንፈስህ
በብርታት ልትቆም ትችላለህ፡፡
ይሄ ትግል ነው፡፡
የታገለ ሁሉ ሊጥል ይችላል፡፡ ሊሰዋም ይችላል፡፡
ይመራል ማለት ግን አይደለም፡፡
መሪ ይሆነኛል ያልከው
(ልምዱ ተቃውሞ መምራት እንደሆነ ብታውቅም)
የሚይዘው የሚጨብጠው ሲጠፋበት
ታግሎ እንደጣላቸው – መሪ ያልሆኑ መሪዎች
በአሱም መንግስት እነሱ የሠሩት ስህተት ሲደገም
ቆይ ችግሩ ግን ምንድን ነበር ብለህ መጠየቅ አለብህ፡፡
መሪዎችህን ከሰከኑት ብልሆች ፈልግ
ሲሞቅ ማቀዝቀዝ፣ ሲቀዘቅዝ ማሞቅ የሚችሉ
ሲበተን መሰብሰብ፣ ሲፈዝ ማንቃት የሚችሉ
ሲጨልም ማብራት የሚችሉ
ከፊት እየሳቡ፣ ከኋላ እየገፉ
ችለው አቻችለው፣ አግባብተው አሳምነው
አዘው ታዘው ሃብትንም፣ ጉልበትንም ተጠቅመው
ወደተሻለ አላማ መውሰድ የሚችሉ
መሪህን ከነሱ ፈልግ፡፡
በአየነዉ ሀይለሥላሴ

Related Post