አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የኮቪድ ወረርሽኝ በሃብታም እና በደሃዉ መካከል ያለዉን ልዩነት እያሠፋዉ ይሆን?

የኮቪድ ወረርሽኝ በሃብታም እና በደሃዉ መካከል ያለዉን ልዩነት እያሠፋዉ ይሆን
የኮቪድ ወረርሽኝ በሃብታም እና በደሃዉ መካከል ያለዉን ልዩነት እያሠፋዉ ይሆን

በስንታየሁ ግርማ – አይረሴዉማርቲን ሊዊተር ኪንግ አንድ ቀን ፍትህ እንደሚሰፍን ህልም አለኝ ብሎ ነበር፡፡ግን ይህ ህልም ቅዥት ሆኖ ዕናዳይቀር ስጋቶች አሁን በስፋት እየታዩ ነዉ፡፡

አልጀዚራ እንደሚለዉ ከሆነ የኮረና መከሰት እና ስጋት ድሃንና ሀብታምን በአንድ ያስተሳሰራቸዉ መስሎ ነበር፡፡ይሁንና ጊዜ እይነጎደ በሄደ ቁጥር ኮርና ድሃን እየጎዳ እና እያደኸየ ፤ሀብታሞች ደግሞ የበለጠ ባለጠጋ እያደረገ ነዉ፡፡ አልጀዚራ ‹‹ወረርሽኙቢሊይነሮችን እየወለደ ድሆችን እየገደለ ነዉ‹‹በሚል ባወጣዉ መጣጥፍ በዚህ ወረርሽኝ ወቅት በየ26 ሰአቱ አንድ ቢሊይነር እየተጠፈጠረ ነዉ፡፡ የአለማች የመጀመሪወቹ 10 ሀብታም ሰወች በእጥፍ ጨምሮል የብልይነሮች ሀብት በዬስከንዱ15000 ዶላር እያደገ ነዉ፡፡

አልጀዚራ አክሎም ኮቪድ 19.99 በመቶ የሚሆነውን የአለም ህዝብ ወደ ድህነት እየከተተዉ ነዉ፡፡ ምንም እንኳ ይፋዊ መረጃወች በኮቪድ የሞቱት ቁጥር 5.5 ሚሊዮን ነዉ ቢሉም አልጀዚራ የሞቾች ቁጥር ከ19 ሚሊዮን በላ ይ እንደሆነ ይገመታል ብሎል፡፡በአብዛኛዉ ደግሞ ድሆች ናቸዉ፡፡ለዚህ ሁሉ መንስኤ እኩልነት እና ፍትሀዊነት አለመሰፍን ነዉ ይላል አልጀዚራ፡፡

ኦክስፋም በበኩሉ ቅጥ ያጣዉ አለመጣጠን በየአራት ሰከንዱ ከሚሞቱት ዉስጥ ለአንዱ ምክነያት ነዉ ይላል፡፡በአብዛኛዉ የሞቱ መንስኤ ደግሞ በድሃ ሀገሮች ያሉ ድሆች ክትባት አለማግኘታቸዉ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክትባቱ የክትባት ቢሊይነሮች እየፈጠረ ነዉ ይላል አልጀዚራ ሰዉ ስራሽ አፓርታይድ እየተፈጠረ ነዉ በሚል፡፡አይኤም ኤፍ በበኩሉ የቢሊይነሮቹ ሃብትናገቢ በአሁኑ ወቅት ባለፉት 14 አመታት ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየጨመረ ነዉ ብሎል፡፡

ለዚህ አለመጣጠን መፍተሄዉ እንደ ባለሞያወች አመለካከት የተላያየ ነዉ፡፡ይሁንና ብዙወቹ እያደገ በሚሄድ የታክስ ምጣኔ (progressive tax rate) ፤ በሃብት እና በንብረት ላይ ታክስ መጣል ፡የታክስ ስወራንን ማስወገድ እና ማጥፋት፡ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መዋጋት ፤ቢዝነስን በ ሞራሊቲ እነዲመራ ማድረግ ብዙዎቹ የተስማሙባቸዉ ናቸዉ፡፡

Related Post