አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን የቀን ውሎ ምን ይመስላል

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን የቀን ውሎ ምን ይመስላል
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ፑቲን የቀን ውሎ ምን ይመስላል

በሱሌማን አብደላ – ቡና ፑቲን የሚወዱት መጠጥ ሲሆን ውሃ ዋና ከቀዳሚ እለታዊ ተግራቸው አንዱ ነው። ፕሬዘዳንቱ የሚመገቧቸው ምግቦች ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ክሪል እርሻ ቦታ የተመረቱ ብቻ ናቸው ዩክሬን የሰሜን ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከጎረቤቷ ጋር ወደ ጦርነት የገባቸው ሩሲያ አሜሪካንን ጨምሮ በምዕራባዊያን አገራት ማዕቀቦች ተጥሎባታል።

ከዚህ ጦርነት ጀርባም ትልቁ ሰውዋነኛው ናቸው። ለመሆኑ ምን አይነት ሰው ናቸው? ጠዋት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ምን ያደርጋሉ? የሚወዱት ምግብስ ምንድን ነው? በአጠቃላይ የፕሬዘዳንቱ የዕለት ተዕለት ውሎ ምን ይመስላል?

ብዙዎቻችን ቀናችንን የምጀምረው በጠዋት ከእንቅልፋችን በመነሳት ቢሆንም ፕሬዘዳንት ፑቲን ከቀኑ ስድስት ሰዓት በፊት አይነቁም። የፕሬዘዳንቱ ረዳቶች እና አብረው የሚሰሩ ባለስልጣናት የግድ ፕሬዘዳንቱ ከእንቅልፋቸው እስኪነቁ፣ ውሃ ዋናቸውን እስኪጨርሱ፣ ቁርሳቸውን እስኪበሉ ድረስ የግድ መጠበቅ አለባቸው።

አይብ ፣የእንቁላል ጥብስ ወይም ገንፎ ከዕለታዊ የቁርስ ማዕዳቸው ላይ አይጠፋም የሚባልላቸው የፍራፍሬ ጭማቂም በጣም የሚወዱት የቁርስ አይነት ነው።
ሁሉንም የምግብ አይነቶች እንደሚመገቡ የሚነገርላቸው ምግብ ከመብላታቸው በፊት በሌላ ሰው ሳያስቀምሱ አይመገቡም።

የሚመገቧቸው ምግቦች ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ጳጳስ ክሪል እርሻ ቦታ የተመረቱ ምግቦችን ብቻም ይመገባሉ። የፕሬዘዳንት ፑቲን የፖለቲካ ረዳት እንደተናገሩት ቡና ፑቲን የሚወዱት መጠጥ ሲሆን ዋና ከመዋኘታቸው በፊት እና ረጅም ጊዜ ሰጥተው የሚያስቡት ጉዳይን ከመጀመራቸው በፊት ይጠቀማሉም ተብሏል።

ትልልቅ ጉዳዮችን ውሃ ውስጥ ሆነው የሚያስቡት በዚህ የረጅም ጊዜ ጠባቂዎቻቸው እና አጃቢዎቻቸው ለአራት ሰዓታት ውጪ ለመጠበቅ ይገደዳሉ።ስራ ከመጀመራቸው በፊት ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ንኪኪ የሌላቸው በዙሪያቸው ያሉ ረዳቶቻቸው ግልጽ የሖኑ የጉዳዮች እና ክስተቶች ማብራሪያዎች እና ጋዜጦች ይቀርብላቸዋል።

ይሄንን የሚያደርጉት የበይነ መረብ ምንተፋዎችን ለመከላከል ሲሆን፤ ሁሉንም ስራዎቻቸውን በወረቀት ላይ የሰፈሩ እና የተጠናቀቁ መረጃዎች ይቀርቡላቸዋል ተብሏል።ፕሬዘዳንቱ በዙሪያቸው ባሉ ረዳቶቻቸው እንዲቀርብላቸው የሚፈልጓቸው መረጃዎች የአገር ውስጥ ዋና ዋና ጉዳዮች፣ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና የፍርድ ቤት ጉዳዮች ናቸው፡፡

የጋዜጦች ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በየዕለቱ ማንበብ የሚፈልጉት እስከ መጨረሻው ድረስ የሚያነቡት ግን በጋዜጠኛ አንድሪ ኮሌስኒኮቭ የሚጻፈው እና ትኩረቱን በእሳቸው ዙሪያ የሚጻፈውን አምድ ብቻ ነው፡፡

ጤናማ የዓመጋገብ ስርዓት የሚከተሉ ሲሆን ቲማቲም፣ ኪያር ወይም ኩኩምበር እና ሰላጣ ከቁርስ ውጪ ባሉ ሰዓቶች የሚመገቧቸው ምግቦች ናቸው።
የበግ ጠቦት ከስጋ አይነቶች መካከል የሚወዱት ፤ አሳ ደግሞ ሌላኛው የሚወዱት የምግብ አይነት ነው ተብሏል።

የቀድሞዋ የፑቲን ሚስት የነበሩት ሊዩድሚላ በእንድ ወቅት እንደተናገሩት ባላቸውን ለማማለል የሚወዱትን ከወተት የሚሰራውን እና በካውካሰስ ተራሮች የሚመረተውን የአልኮል ምርት በብርጭቆ ቀድተው ይጠብቋቸው እንደነበር ተናግረዋል።

Related Post