አርእስተ ዜና
Sat. May 4th, 2024

የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አጠቃቀም

Jan2,2023
የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አጠቃቀምየታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር አጠቃቀም

1. የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጠ ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን በማንኛውም የታክስ ማስታወቂያ ወይም ለታክስ ህግ ዓላማ ሂሳብ በሚቀርብ ወይም ጥቅም ላይ በሚውል ሰነድ ወይም በታክስ ህግ መሰረት በሚዘጋጅ ሰነድ ላይ መግለጽ ይኖርበታል እንዲሁም ታክስ ከፋይ ታክስ ቀንሶ የማስቀረት ግዴታ ባለበት ሰው ክፍያዎች በሚፈጽምለት ጊዜ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን መስጠት አለበት፡፡

2. የንግድ ስራ ለመስራት ፈቀድ ይሰጠው ዘንድ ማመልከቻ የሚያቀርብ ታክስ ከፋይ ፈቃድ ለሚሰጠው ባለስልጣን የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን መስጠት አለበት
3. ታክስ ከፋዩ በተራ ቁጥር ሁለት በተመለከተው መሰረት ፈቃዱን በሚያድስበት ጊዜ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚጠበቅበት የመጀመሪያው የፈቃድ ማመልከቻ ከቀረበ ወዲህ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀየረ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

4. የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ የሚሰጥ የመንግስት አካል ወይም ታክስ ከፋዩ የታክስ ከፋዩ መለያ ቁጥሩን ሳያቀርብ ፈቃድ መስጠት አይችልም፡፡
5. በተራ ቁጥር 6 እንደተገለጸው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ለተሰጠው ሰው ብቻ የሚያገለግል ስለሆነ በሌላ ሰው ጥቅም ላይ ሊውል አይችልም፡፡

6. የታክስ ወኪል የአንድን ሰው የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ሊጠቀምበት የሚችለው
ሀ/ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩ ባለቤት የሆነው ሰው የታክስ ወኪል የታክስ መለያ ቁጥሩን ለመጠቀም እንዲችል በጽሁፍ ሲፈቅድለት፣እና
ለ/ የታክስ ወኪሉ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩን ለታክስ ከፋይ መለያ ቁጥሩ ባለቤት የታክስ ጉዳዮች ብቻ ሲጠቀምበት ነው፡፡
ምንጭ – የገቢዎች ሚኒስቴር

Related Post