አርእስተ ዜና
Sun. Apr 28th, 2024

83 ከመቶ የግል ተቋማት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ወደቁ

Jul16,2023
83 ከመቶ የግል ተቋማት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ወደቁ83 ከመቶ የግል ተቋማት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ወደቁ

ወደ 83 ከመቶ የሚጠጉ የግል ተቋማት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና መዉደቃቸዉን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

ከሰኔ 30 ቀን ጀምሮ ለስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱት 62 ነጥብ 37 በመቶ የመንግስት ተቋማትና 17 ነጥብ 2 በመቶ፣ የግል ተቋማት ተማሪዎች የማለፊያውን 50 በመቶና ከዛም በላይ ውጤት ማስመዝገባችሀዉ ተነገረ። የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ ( ዶ/ር ) ፈተናውን አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

የመውጫ ፈተናውን ከ48 የመንግስት ተቋማት 84ሺ 627 እና ከ171 የግል ተቋማት ደግሞ 109ሺ 239 በድምሩ 194 ሺ 239 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ብቁ ሆነው መመዝገባቸውን ዶ/ር ሳሙኤል አስታውቀዋል። ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ከመንግስት 77ሺ 981 ወይም 92ነጥብ 15 በመቶ ከግል 72ሺ 203 ወይም 65ነጥብ 87 በመቶ በድምሩ 150ሺ 184 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ተናግረዋል። ከመንግስት ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት 48ሺ 632 ተማሪዎች ውስጥ 62ነጥብ 37 በመቶ ከግል ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ ደግሞ 17ነጥብ 2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በመውጫ ፈተናው የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ቅድመ ምሩቃን ተማሪዎች ፈተናውን በየሰድስት ወሩ ደጋግመው መውሰድ እንደሚችሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል። ሚኒስቴር ዴኤታው ኢትዮ ቴሌኮም ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ የዩኒቨርስቲ ምሁራን ፣ የትምህርት ሚኒስቴርና የዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ሙያተኞችና ምሁራን ፣ መገናኛ ብዙሀን፣ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶችና ሌሎችም ፈተናው እንዲሳካ ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

በውስን ተቋማት በጣም ውስን ለሆኑ ሰዓታት ካጋጠመ የሀይል መቆራረጥ እና የኢንተርኔት መቆራረጥ ውጪ በፈተናው ሂደት ችግር አለማጋጠሙንም ዶ/ር ሳሙኤል ጠቁመዋል። የመውጫ ፈተናው ከመሰጠቱ አስቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲለማመዱ የሙከራ (Mock) እና የሞዴል (Model ፈተና እንዲወስዱ መደረጉ ይታወሳል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከጀመራቸው ሪፎርሞች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።

በድሞሩ ለመውጫ ፈተናው ከተቀመጡት 61ሺ 54 ተማሪዎች 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ ማስመዝገባቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።
ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ በ https://result.ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ እንደሚችሉም ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል።

Related Post