አርእስተ ዜና
Sun. Apr 28th, 2024

“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

May29,2021
“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል በመላው ሀገሪቱ ሰላማዊ ሠልፍ ሊካሄድ ነው

“ድምፃችን ለነፃነታችን” በሚል መሪ ቃል በመላው ሀገሪቱ ወጣቶችን ያሳተፈ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተገለፀ።

ሰልፉ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና የሚያሳድሩትን ጫና በመቃወም የሚከናወን ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግስት ከሰሞኑ የጣለው የቪዛ ክልከላና በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ጫና ሀገሪቱ ከድህነት እንዳትላቀቅ ለማድረግ ከመፈለግ የመነጨ በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ለሀገር እድገት የበኩላቸውን በመወጣት የውጭ ጫናን መቃወም ይገባቸዋል ተብሏል።

ይህ ወቅት ህዝቡ ይበልጥ አንድነቱን ሊያጠናክርበት እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን ሊያደበዝዝ እንደማይገባ ተገልጿል።ከምዕራባውያን ጫና ለመላቀቅ መስራት በትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባም ነው የተገለፀው።

መርሐግብሩ ነገ እሑድ ግንቦት 22 በተመሳሳይ ሰአት በመላ ሀገሪቱ የሚከናወን ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Related Post