አርእስተ ዜና
Thu. Dec 26th, 2024

የቀዳማዊት ጽ/ቤት ያስገነባውን የዳቦ ፋብሪካ አስመረቀ

የቀዳማዊት ጽ/ቤት ያስገነባውን የዳቦ ፋብሪካ አስመረቀ
የቀዳማዊት ጽ/ቤት ያስገነባውን የዳቦ ፋብሪካ አስመረቀ

የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ6000 ካሬ ሜትር ላይ ያስገነባው በቀን 1,000,000 ዳቦ የሚያመርት የዳቦ ፋብሪካ ገንብቷል፡፡

217 ሚሊዮን ብር ወጭ የወጣበት ሲሆን ለ450 ሰዎች የስራ እድል የሚፈጥረው ይህ ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ በቀን 72 ቶን ዱቄት ጎን ለጎን ያመርታል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ያስገነባው የዳቦ ፋብሪካ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተገኝተው ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስረክበዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት በቀጣይ በ10 ከተሞች ለሚገነባው የዳቦና ዱቄት ፋብሪካ ግንባታ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡ በነዚህ ከተሞች የሚገነቡት ዳቦ ቤቶች እያንዳንዳቸው በቀን 400 ኩንታል ዱቄት የማምረትና 300,000 ዳቦ የመጋገር አቅም ይኖራቸዋል፡፡

Related Post