አርእስተ ዜና
Sat. Apr 20th, 2024

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን ተመሰረተ

Oct8,2021
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን ተመሰረተየፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን ተመሰረተ

የተመራማሪ፣ መምኅር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ዕረፍት 1ኛ ዓመት መታሰቢያና በስማቸው በተቋቋመው ፋውንዴሽን ምሥረታ ይፋ ማድረጊያ ፕሮግራም በአዘጋጅ ኮሚቴው እና በፋውንዴሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ይፋ ተደርጓል።

በተያዘው መርሃግብር መሠረትም የመታሰቢያ ዝግጅቱ ካሳንቺስ በሚገኘው በቀድሞው ኢንተርኮንቲኔንታል በአዲሱ አጠራር ኢንተርለግዠሪ ሆቴል፣መስከረም 29 ቀን 2014 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄድተገለፀ። የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን ዋና የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ እንደገለፁት ከሆነ‹‹ በዚህ ልዩ የመታሰቢያ ፕሮግራሙ የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን ስምንት አስርተ ዓመታት የተሻገረን ዘርፈ ብዙ የሕይወት ጉዞ በሥነ-ጽሁፍ፣ በዓውደ ርዕይ፣ በሕዝባዊ ውይይትና የእርሳቸውን አስተዋፆዖ በሚያስታውሱ ወጎች ይዘክራል፡፡››

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን ከመንግሥት፣ ከሃይማኖት፣ ከጎሳ ሆነ ከማንኛውም የፖለቲካ አመለካከት ወገንተኛነት ነፃ በሆነ መንገድ መቋቋሙን የገለፁት ዶ/ር በድሉ ድርጅቱ የፕሮፌሰር መስፍንን ምኞትና በጎ ሃሳብ የሚጋሩ ሰዎች ይህንኑ የእርሳቸውን ራዕይና የዕድሜ ልክ ድካማቸውና ሥራቸውን ለማስቀጠል ቤተሰቦቻቸው ጭምር ተሳትፈውበት የተመሠረተ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡ የዚህ ድርጅት ዋና ራዕይ ከችጋርና ድሕነት የተላቀቀች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን እንዲሆን አስተውጽዎ ማድረግ ነው። ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የፋውንዴሽኑ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ አቶ የኔመንግስት ደምሴ በበኩላቸው ፕሮግራሙ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ የተለያዩ እንግዶችን የሚያሳትፍ በመሆኑ እና የኮቪድን ሥርጭት ለመከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአዳራሽ ውስጥ ከሚካሄደው ሥነ ሥርዓት በተጨማሪ በቀጥታ የኦንላይን ሥርጭት በመላው ዓለም እንዲዳረስ በማሰብ ዝግጅቱ የሃይብሪድ ኩነት (Hybrid Event) ቅርፅ ይኖረዋል።›› ሲሉ የፕሮግራሙን ተደራሽነት ይፋ አድርገዋል፡፡

በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ታላላቅ ምኁራን፣ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ሰዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አመራሮች፣ ገጣሚያን፣ የጥበብ ባለሙያዎች፣ የቀድሞ የሥራ ባልደረቦቻቸውና ተማሪዎቻቸው እንዲሁም ሌሎችም አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የሚካሄደውን ልዩ የመታሰቢያ ፕሮግራም በቀድሞው ኢንተርኮንትኔንታል በአሁኑ ኢንተርሌግዠሪ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚከናወንበት ወቅት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ ሚስተር ሀሰን ሺሬ፤ የምስራቅ እና የአፍሪቃ ቀንድየ ሰብዓዊ መብትተሟጋቾች ጥምረት ሊቀመንበር፣ አቶ መለስካቸው
አምኃ የኢሰመጉ ሊቀመንበር እና አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ፣ ፕሮፌሰር ደሳለኝ ራኽማቶ የመግቢያ ንግግር እና ጥናታዊ ወረቀትን በዚሁ ፕሮግራም የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

በመታሰቢያ ፕሮግራሙ በተለይ ‹‹ሰላምና የግጭት አፈታት ተሞክሮዎች፟ በኢትዮጵያ፣ የፕሮፊሰር መስፍን የሰላማዊ ትግል መርሆዎችና ምላሽ ያላገኙ የሰላም ጥሪዎች›› የሰብአዊ መብቶች፤ የህግ የበላይነት እና የማህበራዊ ፍትሕ መከበር ጥያቄ በኢትዮጵያ (የኢሰመጉልደት፤ እድገት፡ ተጋድሎና የፕሮፌሰርመስፍን ሚና)፣ ኢትዮጵያን ከድህነትና ከችጋር ለማላቀቅ የተደረጉ ጥረቶችና ቀጣይ ተግዳሮቶች፣ በሚሉ ጥናተዊ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ የሆነ ውይይት ይካሄዳል፡

Related Post