አርእስተ ዜና
Sat. May 4th, 2024

ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት አቇርጠዋል

Sep22,2020
ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት አቇርጠዋልከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ትምህርት አቇርጠዋል

ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከ26 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎችን አስመልክቶ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳቡን ያቀረቡት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ እንዳሉት በቫይረሱ ምክንያት በተለይም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱን ወደ መደበኛ ስራቸው ለመመለስ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጀመሩ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ አበባ ቫይረሱ በስፖርቱ ዘርፍም እንቅስቃሴዎችን በመገደቡ ምክንያት ሃገራችን ከአለምና ከአህጉራዊ ዉድድሮች ውጭ ልትሆን እንደምትችል አብራርተዋል፡፡

ቫይረሱን እየተከላከሉ ስልጠናዎችንና ዉድድሮችን ለማስቀጠል የሚያስችሉ መመሪያዎች ተዘጋጅተው በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የቅደመ- ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ሰብሳቢዋ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

Related Post