አርእስተ ዜና
Tue. Apr 30th, 2024

ከ151 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Sep25,2022
ከ151 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉከ151 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከመስከረም 6 እስከ 12 2015 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 144 ነጥብ 1 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ በአጠቃላይ 151 ሚሊዮን 287 ሺህ ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዳማ፣ ሞያሌ፣ እና አዋሽ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 34 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ 28 ነጥብ 1 ሚሊዮን እና 21 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 23 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Related Post