አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል አወጀች

ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል አወጀች
ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል አወጀች

በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ መካከል የሚካ ሄደውን ጦርነት መባባስ ተከትሎ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአማራ ክልል አወጀ።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የተከለከሉ ተግባራት ምንድናቸው?
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች
የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ የዚህን አዋጅ አላማ ለማሳካት አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፦
1) የአደባባይ ስብሰባና ሰልፍ ማድረግ፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስን የመከልከል፣
2) የሰዓት እላፊ የማወጅ፤ ለተወሰነ ጊዜ አንድ መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋም መጓጓዣ ዘዴ እንዲዘጋ እና እንዲቋረጥ ለማዘዝ፣
3) ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቁ ለማዘዝ፣

4) የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስን ለመከልከል፣
5) በሀገረ መንግስቱ እና በህገ መንግስታዊ ሥርዓቱ ላይ የሚቃጡ ወንጀሎችን እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመጣስ እና አፈፃፀሙን የማደናቀፍ ወንጀልን መፈፀሙ፣ መሞከሩ ወይም ለመፈፀም በዝግጅት ላይ መሆኑ የተጠረጠረ ማናቸውንም ሰው ያለ ፍርድ ቤት ትአዛዝ በቁጥጥር ስር በማድረግ ለማቆየት፣
6) ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ወይም ሊፈፀምባቸው እንደሚችል የተጠረጠሩ እቃዎችን ለመያዝ ሲባል
ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በየትኛዉም ጊዜ ማናቸውንም ስፍራ እና መጓጓዣ ለመበርበር፣

7) መንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማትና የመሰረተ ልማቶች ጥበቃ ሁኔታን ለመወሰን፣
8} ማናቸውም ከዚህ አዋጅ አላማ በተፃረረ መልኩ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የተጠረጠሩ የመገናኛ ብዙሃንም ሆነ ሌሎች አካላት አንዲዘጕ፣እንዲቋረጡ፣ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ወይም እንቅስቃሴያቸው እንዲገደብ ለማዘዝ፣
9) ማንኛዉም አገልግሎት መስጫ ተቋም እንዳይዘጋ እና ለህዝብ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማዘዝ፣

10) ማንኛዉም የህዝብ ትራንስፖርት መስጫ ተሸከርካሪዎች እና ማጓጓዣ እቃዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ለማዘዝ፣
11) የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እና መዋቅሮችን መልሶ ማቋቋም፣ ማደራጀት ወይም የአስተዳደር እና የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ እና ሌሎች እርምጃዎችን የመውሰድ፣
12) የህዝብን ሰላም፣ የሃገር ደህንነትን አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን የመዉሰድ፣ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ እና ትእዛዝ የመስጠት ስልጣን አለዉ፡፡
የተከለከሉ ተግባራት እና ግዴታዎች
1) ማንኛውም ሰው ይህንን አዋጅ፣ በአዋጁ መሰረት የሚወጡ መመሪያዎችን፣ የሚሰጡ ትዕዛዞች እና የሚተላለፉ ውሳኔዎችን የመተግበር አና የማክበር ግዴታ አለበት።
2) የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አላማ የሚቃረን፣ የሚቃወም እና በክልሉ የአመጽ እንቅስቃሴን የሚያበረታታ፣ ሰላማዊ ዜጎችን የሚያሸብር፣ እንዲሁም የፀጥታ መደፍረሱን የሚያባብስ ንግግር፣ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ቅስቀሳ በማንኛውም መንገድ ማድረግ ወይም ማሰራጭት የተከለከለ ነው።

3) በየትኛውም መንገድ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለታጣቂ ቡድኖች የገንዘብ፣ የመረጃ፣ የቁስም ሆነ የሞራል ድጋፍ ማድረግ የተከለከለ ነው።
4) ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም የአደባባይ ስብሰባ ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ማድረ የተከለከለ ነው።
5) ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ፈቃድ ውጭ ማናቸውንም የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
6) ማንኛውንም ወሳኝ በሆነ የአገልግሎት ዘርፍም ሆነ በምርት ሂደት ላይ የስራ ማስተጓጎል ወይም የኢኮኖሚ አሻጥር መፈፀም የተከለከለ ነው።
7) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ሰበብ በማድረግ የግል ጥቅም ለማግኘት ስልጣንን አላግባብ መጠቀም፣ምክንያታዊ የሆነ ጥርጣሬ ሳይኖር ሆን ብሎ ዜጎችን ማሰር ወይም መሰል እርምጃ መውሰድ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
https://youtu.be/EnXX1O6C6Os

Related Post