አርእስተ ዜና
Mon. May 6th, 2024

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ልማት ዕድገት ቀዳሚ መሆኗ ተገለፀ

Nov7,2023
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ልማት ዕድገት ቀዳሚ መሆኗ ተገለፀኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ልማት ዕድገት ቀዳሚ መሆኗ ተገለፀ

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ልማት ዕድገት ቀዳሚ ከሆኑ ሀገራት ውስጥ አንዷ መሆኗን የዓለም ቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ገለፀ፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ 15 ሀገራት በዓለም አቀፍ ጎብኝዎች ፍሰት በዋናነት ጥቅል የቱሪዝም ልማት (የመዳረሻ ልማት፣ ሰው ሀብት ልማትና አገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች) የላቀ ውጤት እንዳስመዘገቡ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ከ2019 ወዲህ የተፈጠረውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ የነበረ መሆኑን ጠቅሶ ዘርፉ በ2023 የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከፍተኛ መሻሻልሎች ማሳየቱን ገልጿል፡፡ በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት ከጃኑዋሪ እስከ ጁላይ ባለው ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ፍሰት የ28 በመቶ እድገት ያሳየች ሲሆን በአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በዓለም ደግሞ 7ኛ ደረጃን መያዟ ተረጋግጧል፡፡

የዓለም ቱሪዝም ድርጅት በሪፖርቱ ከዘረዘራቸው 15 ሀገራት ውስጥ በአፍሪካ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ ታንዛኒያ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ እንደ ድርጅቱ ገለፃ ከሆነ ኢትዮጵያን ጨምሮ እነዚህ 15 ሀገራት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ዓለም አቀፍ ቱሪዝሙ በማነቃቃት ላይ እንደሚገኙ አፅዕኖት ሰጥቷል፡፡

ይህ በሀገር ደረጃ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ እየተደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል የሚያስችል እና ለዘርፉ የወደፊት ዕድገትም ተስፋ ሰጭ ነው።
ድርጅቱ Tourism Barometer በተሰኘ የመረጃ ምንጩ ዓለም አቀፍ የጎብኝዎችን ፍሰትና ተያያዥ መረጃዎችን አስመልክቶ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርቶችን እንደሚያወጣ ይታወቃል፡፡

Related Post