አርእስተ ዜና
Wed. Nov 13th, 2024

በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ

በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ጨረታ ያሸነፈው “ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ” የስራ ፈቃድ አገኘ።
በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ ያገኘው ግሎባል አሊያንስ ፎር ኢትዮጵያ የተባለው ኩባንያ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
የስምምነት ፊርማው የተከናወነው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡት የኬኒያው ፕሬዝዳነት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት ነው።
የኢትዮጵያ ኮሙንኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ፤ ከቮዳኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ሻሚል ጆሱ፣ ከሳሪ ኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ኢድግዋ እንዲሁም ከሲሚቶሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ ማይሽ ማሂሽታ ጋር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
ኩባንያው ጫረታውን ያሸነፈበትን 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን የኢትዮጵያ ከሚዩኒኬሽን ባለስልጣን መግለፁ ይታወቃል።
በዛሬው እለት ደግሞ ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን ፈቃድ ያገኘበት መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የኬኒያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ በተገኙበት በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ተካሂዷል።
ግሎባል ፓርትነር ፎር ኢትዮጵያ የኬኒያው ሳፋሪ ኮም፣ የዩናይትድ ኪንግደም ቮዳፎንና ሲዲሲ ግሩፕ፣ የደቡብ አፍሪካውን ቮዳኮም የጃፓኑን ሲሚቶምና ዲኤፍሲን በጥምረት የያዘ ኩባንያ ነው።
ኩባንያው በቀጣይ አስር ዓመታት ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
በዚህም ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1 ቀን 2013 (ኢዜአ)

Related Post