አርእስተ ዜና
Fri. Apr 26th, 2024

ከ109 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Jun16,2021
ከ109 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉከ109 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ባሳለፍነው ሳምንት ከ109 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና የወጭ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባሳለፍነው ሳምንት ባደረገው ክትትል 109 ሚሊዮን 384 ሺ የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 427 ሺ 950 ብር በላይ የሚያወጡ የወጭ ኮንትሮባንድ እቃዎች በ13 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አዲስ አበባ ኤር ፖርት ፣ አዋሽ እና ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 60 .5 ሚሊዮን ፣ 13.6 ሚሊዮን 11.1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል ፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በመከላከያ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ናቸው፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ መድሀኒት ፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎችና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡ የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ አምስት ግለሰቦች እና 64 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች ፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት ምስጋናችንን እናደርሳለን፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
(ምንጭ – የጉምሩክ ኮሚሽን)

Related Post