አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈፀ።

በጌዴኦ ዞን በይርጋጨፌ ወረዳ በቆንጋ ቀበሌ በተከሰተው የትራፊክ አደጋ በሰዉና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል። ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ይጓዝ የነበረው 45 ወንበረ ያለዉ የሰሌዳ ቁጥር ኦሮ ኮድ-3 34983 የሆነ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ በሰዉና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።



በተከሰተው የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ13 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የይርጋጨፌ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ታምራት ምትኩ ገልጸዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በይርጋጨፌና በዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአደጋ መንሴ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

(ምንጭ – የጌዴኦ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

Related Post