አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ለኢትዮጵያ ረዳ

የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ለኢትዮጵያ ረዳ
የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ለኢትዮጵያ ረዳ

የዓለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ተጨማሪ ሶስት ሄሊኮፕተሮችን ለኢትዮጵያ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን እና በኢትዮጵያ አለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ተወካይ ፋጡማ ሰይድ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት የርክክብ ስነ ስርዓት በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ተካሂዷል፡፡

በአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት ድጋፍ የተገኙት እነዚህ ሶስት ሄሊኮፕተሮች የበረሃ አንበጣ አሰሳ ስራን በማቀላጠፍ እና በጥቂት ጊዜ ዉስጥ ሰፊ ቦታ የሚሸፍን አሰሳ በማድረግና ተባዩን በመከላከልና በመቆጣጠር በግብርና ምርት ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት ከመቀነስ አኳያ ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡

የበረሃ አንበጣን በመከላከል ረገድ ድርጅቱ ካሁን በፊትም ለኢትዮጵያ ሁለት የኬሚካል መርጫ አዉሮፕላኖች እና የኬሚካል፣ የተሸከርካሪዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

(ምንጭ – የግብርና ሚኒስቴር)

Related Post