አርእስተ ዜና
Fri. Apr 19th, 2024

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ11 ሺህ ሰዎች ድጋፍ አደረገ

Apr18,2020
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ11 ሺህ ሰዎች ድጋፍ አደረገየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ11 ሺህ ሰዎች ድጋፍ አደረገ

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለየክልሉ ና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከ11 ሺህ በላይ ለሆኑ ደሀና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጉሙሩክ ኮሚሽንና ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የተገኙ የአልባሳት ድጋፎችን በሁሉም ክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ የሠራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮዎች አማካኝነት ከ11 ሺህ በላይ ለሆኑ ደሀና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች የአልባሳት ድጋፍ አደረገ::

በአገራችን በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ በርካታ ዜጎች አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ ልጅ/ልጆች የያዙ እናቶች እና አረጋዊያን ተጠቃሾች ናቸው ያሉት የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ይህን ችግር ደረጃ በደረጃ ለመቀነስ እንዲያስችል በጥናት ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት መንግስት ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር በ11 ዋና ዋና ከተሞች በሚተገበረው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ውስጥ ኑሮና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 22,000 ዜጎች በፕሮግራሙ እንዲታቀፉ አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለው እንደገለጹት ፕሮግራሙ በሚሸፍናቸው 11 ከተሞች የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ውል ለፈረሙ ድርጅቶች አልባሳት እንዲሰጣቸው በማድረግ ላይ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ለአዲስ አበባ ፤ለኦሮሚያ፤ለደቡብ ፤ለትግራይ፤ለሐረሪ ፤ለድሬዳዋ ፤ለአማራ ፤ለጋምቤላ ፤ ለሶማሌ ፤ ለአፋር፤ ለበቤኒሻጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤቶች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አማካኝነት በከተሞች ውስጥ ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲደርሳቸው ተለግሷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማስተባበር በ 8 ከተሞች በ1ኛ ዙር 6,295 ህፃናት በ22 ደርጅቶች ህፃናት ከጎዳና እንዲያነሱ በማደረግ ላይ ሲሆን በ4 ከተሞች 3,204 ያህል አረጋዊያን ፣ በ5 ከተሞች 1380 ልጅ የያዙ እናቶች፣ በ4 ከተሞች 842 ወጣቶች ከጎዳና ላይ በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተነስተው በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ በማድረግ ዘላቂ ህይወታቸውን ለማሻሻል ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሮማን ገብረ ስላሴ በበኩላቸው የአልባሳት ድጋፉ በዚህ ወቅት መደረጉ አጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ የሚኒስቴር መስሪያ ቤትን አመስግነው ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

በርክክቡ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያና ያዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎች በበኩላቸው ልግሳውን አመስግነው ድጋፉ ለታለመላቸው የህብረተሰብ ክፍል እንደሚደርስም ገልጸዋል፡፡

(ምንጭ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር)

Related Post