አርእስተ ዜና
Fri. May 3rd, 2024

በባህር ዳር የብረታብረት ፋብሪካ ማምረት ጀመረ

May29,2021
በባህር ዳር የብረታብረት ፋብሪካ ማምረት ጀመረበባህር ዳር የብረታብረት ፋብሪካ ማምረት ጀመረ

በ800 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል እየተገነባ የሚገኘው ራቫል ስቲል ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫ የተሰበሰቡ ቁርጥራጭ ብረቶችን በግብዓትነት በመጠቀም ብረት ማምረት ጀመሯል፡፡

በአራት የግንባታ ምዕራፎች ተከፍሎ እየተገነባ የሚገኘው “ራቫል ስቲል ማኑፋክቸሪንግ” ፋብሪካ ለግንባታ ግብዓት የሚሆን ፌሮ ብረት ማምረት የሚስችለውን የመጀመሪያውን የብረት ምርትና ለህክምና የሚያገለግል ኦክስጅን ማምረት መጀመሩን የፋብሪካው የሰው ኃብት መምሪያ ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ አርቄ ተናግረዋል፡፡

ራቫል ብረታ ብረት ፋብሪካ አሁን ላይ በሦስት ፈረቃ የሚሰሩ ከ500 በላይ ሰራተኞች እንዳሉት የገለጹት አቶ መንግስቱ የፋብሪካው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ 10ሺህ ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞችን የስራ ዕድል ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ አክለውም ፋብሪካው ሁለተኛ የግንባታ ምዕራፍ ላይ በመሆኑ በ2014 ዓ/ም መስከረም ላይ ፌሮ ብረት ማምረት እንደሚጀምር እና ለሐገር ውስጥ ገበያ እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡

የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪጅ ሚስተር ሻም ራቭል በበኩላቸው ፋብሪካው ከ3 ዓመት በፊት በክልሉ የኢንቨስትመንት ፈቃድ አግኝተው ግንባታ በመጀመራቸው እና በመንግስት በኩል እየተደረገላቸውን ስላለው ድጋፍ አመስግነው ፋብሪካው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዳይጠናቀቅ የሲሚንቶ እጥረት እንደገጠማው ተናግረዋል፡፡

(አማራ ኮሙዩኒኬሽን)

Related Post