አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

የሳይንቲስቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ሙግት

የሳይንቲስቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ሙግት
የሳይንቲስቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ሙግት

በመኮንን ተሾመ ቶሌራ (Science Writer) – ከሀገራችን ምሁራን መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ተወልደብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ሰሞኑን “ግልፅ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ መንግስት” በሚል ርእስ የፃፉትን ፅሁፍ አነበብኩት። እሳቸዉ በፅሁፋቸዉ አበክረዉ ለማስረዳት እንደሞከሩት በሀገራችን ኢትዮጵያ በእፅዋት ስነምህዳር (Plant Ecology) ዘርፍ ካሉን ታላላቅ ምሁራን አንዱ ናቸዉ። ይሁንና አሁን የፃፉትን ፅሁፍ ባለኝ አቅም ካነበብኩት በኋላ ፅሁፉ የሳችዉን ሳይንቲስትነት የሚመጥንና በሳይንሳዊ አመክንዮ የተደገፈ ሳይሆን በአብዛኛዉ ህይወታችዉን የፈጁበትን “የአካባቢ ጥበቃ” ፍላጎት መገለጫና ሳይንሳዊ ያልሆነ ሙግት ሆኖ ግኝቸዋለሁ።

በፅሁፋቸዉ ያነሱት ዋነኛ ነጥብ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የግብርና ምርትን ለማዘመንና ለማሻሻል የባዮቴክኖሎጂ በተለይም በዘረ መል ምህንድስና (Genetics Engineering) በተወሰነ መልኩ ለምሳሌ በጥጥ ምርት ላይ በጥንቃቄና የደህንነተ ህይወት መርህ በመከተል የጀመረችዉ እንቅስቃሴ ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ የተፈፀመዉን የካርታኼና የደህንነተ ህይወት ዓለም አቀፍ ፕሮቶኮል ስምምነትን የሚጥስ ነዉ የሚል ነው።

እንደሳቸዉ ባሉ “የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች” እና በባዮቴክኖሎጂ አዋቂዎች መካከል በዘረ መል ምህንድስና ዙሪያ የሚደረገዉ ክርክር ረዘም ያለ ታሪክ ያለዉ ሲሆን ብዙ ጊዜ ክርክሩ የሚደረገዉ እዉነታና ሳይንሳዊ መረጃዎች ላይ ብቻ አተኩሮ ሳይሆን በየዘርፎቹ ዙሪያ ባሉ ልዩ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ብዙዎች ይጠቅሳሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ተወልደብርሃን ባላቸዉ ልምድ ልክ ሳይንሳዊ ትነታኔ ያሳዩበት ሳይሆን “የአካባቢ ጥበቃ” ፍላጎታቸዉን ያንፀባረቁበት ይመስለኛል። ለዚህም በርካታ ምክንያቶቹን መጥቀስ ይቻላል።

በመጀመሪያ ደረጃ አስፈላጊ ጥንቃቄ በማድረግ የዘረ መል ምህንድስና ቀስ በቀስ በተለይ በጥጥ ላይ የመጀመሩ ጉዳይ አሁነ የተጀመሩ ሳይሆኑ ዶ/ር ተወልደብርሃን የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን እየመሩ እያለ የተጀመረ በመሆኑን ዛሬ በመሰረቱ የተለየ ነገር የለም።

ሌላዉ የካርታኼናውን የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ዓላማ “በዘመናዊ ዘረ መል ምህንድስና የሚሰሩት ልውጥ ህያዋን ጉዳት በማያመጣ መልኩ በጥንቃቄ እንዲያዙ፣ እንዲጓጓዙና በጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ነው” በሚለዉ መሰረት ሀገራችን የኢትዮጵያም ይህንኑ በፅኑ ተከትላ እየሰራች እንጂ እስካሁን የተፈጠረ ችግር የለም።ዶ/ር ተወልደብርሃንም ከዚህ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ችግር ዙሪያ ምንም አይነት መረጃ አላቀረቡም።

ተጨባጭ መረጃ ከማቅረብ ይልቅ እሳቸዉ “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት የካርታኼናውን የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮል ሕጋዊ ትግበራ ገሸሽ እያደረገው ከሆነ፤ ሀገሪቱ ዓለምአቀፍ ስምምነትን እየጣሰች መሆኑ ግልፅ ይሆናል።” በማለት የተለመደዉን “የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪነታቸዉን” ገልፀዋል።

በርግጥ ዘረመሎች (ዲ•ኤን•ኤ) የሕያዋን ባሕርያትን ይወስናሉ። ቁመናን ፣ ቀለምን ፣ ቅርፅን ወ•ዘ•ተ።ይህም የሚሆነዉ ከሁለት ወላጆች የአንድ ዝርያ /ስፖሺስ/ አባላት የሆኑ ዘረመሎች በምህንድስና ልዉዉጥ ሲካሄድ ነው። ከዘመናችን ምጡቅና ድንቅ ቴክኖሎጂዎች መካከል ዋነኛው የዘረመል ምህንድስና መሆኑ ይታወቃል። ዘርፉ ዘረመሎችን ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ለማሸጋገር አስችሏል። የዘረመል ምህንድስና የሕያዋንን ባሕርይ ስለሚነካካ የሕይወትን መሠረት ሊለውጥ ይችላል። ይህም የባሕርይ ለውጥ መሻሻልም ወደ መጥፋትም ሊያመራ ይችላል።

ይሁንና ዘመናዊዉ የዘረ መል ምህንድስና አለምን የሚያጠፋ ሰይጣናዊ ምትሀትም ወይም አለምን የሚያድን የመላእክት ስራም ሳይሆን እራሱን የቻለ ሳይንሳዊ ጥበብ ነዉ። እንደብዙዎቹ ሳይንሳዊ እንቅስቃሴዎች በጥንቃቄና በጥበብ ከተጠቀምንበት እጅግጠቃሚ የሆነ ሳይንስ ነዉ።

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን የዘረ-መል ምህንድስና ውጤቶችን ለመጠቀም የሚደረገው ጥረት በአካባቢና በብዝሀ-ሕይወት ሀብቶች ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉ ጠንቆችን በጥብቅ ቅድመ ጥንቃቄ እየተሠራ ነዉ ። ለዚህም ኢትዮጵያ የደህንነተ ሕይወት የህግ ስርዐትን በአዋጅ ቁጥር 655/2009 (በአዋጅ ቁጥር 896/2015 እንደተሻሻለው) አውጥታ መተግበሯን ገልፀዋል።

ይሄ ህግ የደህንነተ ህይወት ህግጋት ልውጠ ህያዋን (GMOs) ወይም የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች በሚመረቱበት፤ በሚዘዋወሩበት፤ በሚጓጓዙበት፤ በሚከማቹበት እና ለምርምርና ለማስተማር በሚውሉበት ወቅት በብዝሀ ሕይወትና በአካባቢ ላይ ጠንቅ እንዳያስከትሉ ለማድረግ የተዘጋጁ የህግ ማዕቀፍ ነዉ።

ልክ የኒኩሊዬር ሀይል በጥንቃቄ ከተያዘ ለሃይል ማመንጫነት፣ ግዙፍ ማሽኖችንና ኢንዱስትሪዎችን ለማንቀሳቀስ እንደሚጠቅመዉ ወይም በተቃራኒዉ ለጥፋት እንደሚዉለዉ።

ወይም ደሞ ሌሎች ጠቃሚ ነገሮችን ገና ለገና ጉዳት ያመጣሉ ብለን መተዉ እንደሌለብን ወሳኝ ነገሮች። “ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም !” እንደሚሉት ። ለምሳሌ ገና ለገና አዉሮፕላን ይከሰከሳል ብለን ከመጓዝ እንደማንታቀበዉ ፣ ገና ለገና ሁሉም መዳኔቶች የጎንዮሽ ጉዳት አናቸዉ ብለን ክኒን አንዉጥም እነደማንለዉ ፣ ገና ለገና ልንሞት እንችላለን ብለን በሀኪሞች ቀዶ­ጥገና አንደረግም እንደማንለዉ ወ•ዘ•ተ።

የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ ልክ በብዙ ሀገሮች እየተስፋፋ እንዳለዉ በእኛም ሀገር አቅም በፈቀደ መጠን እና ሁሉንም “የደህንነተ ህይወት” (Bio Saftey) ጥንቃቄዎችን በጠበቀ መልኩ እንዲያድግ የምንፈልግበት ምክንያት ሳይንሱ ልክ እንደሌሎቹ ሳይንሶች ሁሉ በጥንቃቄ ካልተሰራ ምንም አይነት ጉዳት የለዉም ብለን ሳይሆን ሳይንሱ በግብርና፣በህክምና፣በኢንዱስትሪ እና በሌሎች በርካታ ዘርፎች ያለዉ ጠቀሜታ እጅግ ጠቃሚና አስደናቂ በመሆኑ ነዉ።

ስለዚህ እንደነ ዶ/ር ተወልደብርሃን ያሉ “የአካባቢ ጥበቃ ጠበቆች” ነን የሚሉግለሰቦች የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስን ሚዛናዊና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከማየት ይልቅ የራሳቸዉን ፍላጎትና ምኞት ብቻ ማየታችዉ ተገቢ ካለመሆኑ በተጨማሪ ሀገርንም የሚጎዳ ነዉ። የምርምር አቅማችንንም የሚያዳክመ እንደሆነ የዘርፉ ምሁራን የሚስማሙመት ጉዳይ ነዉ። ለምሳሌ ቀደም ሲል የመለስ ዜናዊ መንግስት በነዶ/ር ተወልደብርሃን አማካሪነት ያወጣዉ የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን መመርያ እና “የስነ­ህይወት” ህግ እንቅፋት ለተመራማሪዎችና ሳይንቲስቶች እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ2002 ዓ.ም ባወጣዉ የባዮ ሴፍቲ አዋጅ መሰረት የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አዋጁ የሚተገበርበትን መመርያ አውጥቷል፡፡ ነገር ግን በጄኔቲክ ምህንድስና የተዳቀለ ጥጥ መጠቀም የሚፈልጉ የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ሕጉን ተችተዋል፡፡

የምርምር ባለሙያዎችም እንደሚሉት፣ ለምርምር የገባን ልውጥ ዘር ላይ በሚያደርጉት የምርምር ሒደት ችግር ቢፈጠርና ዘሩ ቢያፈተልክ እስከ 15 ዓመት እስራት እንደሚቀጡ ተደንግጓል፡፡ ‹‹ይህ አስፋሪ ነው፤ ነፃነት አይሰጥም፡፡ ምርምር ነፃነት ይፈልጋል፤›› ብለዉ ነበር፡፡

ዛሬ በአለማቸን የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስን የሚያስፋፉና በሳይንሱም የተመረቱ የግብርና ምርቶችን (Biotech Crops) ፣ የህክመና መድሃኒቶችንና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የሚጠቀሙ ሀገራት ቁጥር እጅግ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ይህመ የሚሆነዉ በብዙምክንያቶች ነዉ፦

1. የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ እና “የደህንነተ ህይወት” ስራ እየዘመነ መምጣቱና
በአሁኑ ወቅት የዘረመል ምህንድስና እና synthetic biology ዘርፍ በተለያዩ የኮምፒዉተር ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ቆየት ካለዉና እነ ዶ/ር ተወልደብርሃን ከተማሩበት ዘመን በተለየና በፈጠነ መልኩ እየዘመነ መቷል፡፡

ለምሳሌ ዛሬ የዘረመል ምህንድስና ሳይንቲስቶች እንደ ክሪስፐር (CRISPR) ሞለኪዩል ያሉ ዘዴዎችን በመጠቀም የዘረ መል ምህንድስናን ፍፁም በሚባል ደረጃ በጥራት በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ክሪስፐር የተሰኘዉ ሞለኪዩል ባለሙያዎቹ በአንድ ሴል ክሮሞዞም ዉስጥ የሚገኙትን እያንዳንዱን የዲ ኤን ኤ የሞለኪውል አንጓዎችን በሚገባ በመለየት እና ካስፈለገም ለይቶ ቆርጦ በማዉጣት በሚፈለግ መልኩ አንጓዎችን በማስተካከር ተፈላጊዉን የዲ ኤን ኤ ለዉጥ ለማረግና ተፈላጊዉን ዉጤት ለማመጣት አስችሏቸዋል፡፡

በቤተ ሙከራና በተከለለ ከባቢ የሚደረጉ የመስክ ጥናቶች (Confined field trial) እንዲሁም የካርታኼናው የደህንነተ ህይወት ፕሮቶኮልና በሌሎች ተመሳሳይ አገራዊ ህጎችና መመሪያዎችም አፈፃፀም በተለያዩ ሳይንሳዊ ዘዴዎቸ እየዘመኑና ይበልጥ አስተማማኝ በሚባል ደረጃ እያደጉ በመምጣታቸዉ የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስን ተፈላጊነት አየጨመሩት፡፡

በሀገራችን ደህንነተ ህይወት(Biosafty) የብዝሀ ሀብቶችን ምህንድስና(Biotechnology) ውጤቶች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ታስቦ የዘረ መል ምህንድስና የተካሄደባቸው ውጤቶች በአካባቢና በብዝሀ ህይወት ሀብት ላይ ሊኖራቸው የሚችልን አሉታዊ ተፅኖ ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት በቅድመ ምርምር፣ በምርምር ወቅትና ከምርምር በኋላ በሚኖሩ የስርፀት ጊዜያት የሚከናወን ሳይንሳዊ የክትትልና ቁጥጥር ስርዐትም ተዘርገቷል።

2. ግሎባላይዜሽን
በዘነናችን የሀገራት ኢኮኖሚ በእጅጉ የተሳሰረና የተቀራረበ ነዉ፡፡ የሰዎች ዝዉዉርና የንግድ ልዉዉጡም ከምን ጊዜዉም በላይ ሰፍቷል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ በአለማችን በስፋት እየተመረቱ የሚገኙት የዘረ መል ምህንድስና ዉጤቶች ከአንድ ሀገር ወደሌላኛዉ በቀላሉ የሚገቡበት እድልም በጣም ሰፊ እየሆነ ነዉ፡፡

ለምሳሌ ከሀገራችን ጎረቤቶች መካከል እንደ ኬንያ ያሉት ሀገራት የዘረ መል ምህንድስና ዉጤት የሆኑ ሰብሎችን በብዛት እየተጠቀሙ ነዉ ፡፡ የኛና የኬንያ ዜጎች በድንበር በኩል ሰፊ ግንኙነት ያላቸው እና እርስ በርስም በንግድና ማህበራዊ ትስስር የሚያደርጉ እነደሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ሰፊ ግንኙነት የዘረ መል ምህንድስና ዉጤቶችን በቀላሉ ለመቀያየር ይሚያችል እንደሆነና ለቁጥጥርም አስቸጋሪ እንደሆነ ይነገራል ፡፡ ስለዚህ የዘረ መል ዉጤቶችን እስከዛሬም ሀገራችን እንጋይገቡ የተደረገዉ ክልከላ ምን ያህል ዉጤታማ ነበረ ብለንም መጠየቅ ይገባናል፡፡

በተጨባጭም ከዚህ በፊት ከልውጥ ህያዋን (GMOs) የተሰሩ የምግብ ዘይቶችና ሌሎቸም ምርቶች ሀገራችን ገብተዉ በሚዲያም ጭምር ሲነገር ደምተናል፡፡ አሁንስ ምን ያህል የቁጥጥር አቅምና የሰለጠነ የሰዉ ሃይል አለን ብሎ ማየቱም ጥሩ ነዉ፡፡

3. የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ ከጉዳቱ ጥቅሙ መብለጡ (Misconceptions amd myth)
ሌላዉ ብዙ ሰዉ የማይገነዘባችዉና ስለ ልውጥ ህያዋን (GMOs) የሳሳቱ አተመለካከቶች በአለም ላይ ብዙ መሆናቸዉና “የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች” ደሞ ይህንኑ አላዋቂነት ሆን ብለዉ ማራገባቸዉ ትልቅ የሳይንስ እንቅፋት ነዉ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ (COVID-19)

ዙሪመ “የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች” ገና ቫይረሱ ከየት እነደመጣ ሳይታወቅ ሰዎች በላቦራቶሪ የሰሩት ነዉ በማለትና እረዣዥም ፅሁፍ በመፃፍ ለማጭበርበር ሲሞክሩ አስተዉለናል ፡፡ ለማንኛዉም የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ ዙሪያ ስላሉ የሳሳቱ አተመለካከቶች ለምሳሌ የሚከተሉትን እንይ፦

 ባለፉት አስር እና ሀያ ሺሀ አመታት ገበሬዎች በራሳቸዉ መንገድ ሳያዉቁተ የብዙ እፅዋት ዝርያዎችን የዘረ መል ቀይረዋል
 የዘረ መላቸዉ የተስተካካለ እፅዋትን መመገብ የሰዎችን የዘረ መል ይቀይራል ብሎ ማመን ግኙም የተሳሳተ ነዉ
 የዘረ መል የተስተካካሉ እፅዋትን ዘር መልሶ መጠቀም አይቻልም የሚለዉ የተዛባ ሀሳብ ነዉ
 የዘረ መል ቴክኖሎጂ ጠቅላላ አላማ የአለማቀፍ ግዙፈ ኩባንያዎች ጥቅመ ማስከበሪያ እንጅ ለልማት የሚበጅ ታላቅ ሳይንስ እንዳልሆነ ማሰብ
 የዘረ መል ቴክኖሎጂ በበቂ ሁኔታ ገተሻና ማረጋገጫ አይደረገበተም ብሎ ማሰብ
 የዘረ መል ቴክኖሎጂ ከተፈጥሮ የራቀ አድርጎ ማሰብ
 በዘረ መል ቴክኖሎጂ የተመረቱ ምግቦች በቂ ንጥረ ነገር የላቸዉም ብሎ በተሳሳተ መንገድ ማሰብ
 ባጠቃላይ የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ ሳይንስ ሳይሆን ጭራቅ አስመስሎ ማቅረብ ወ•ዘ•ተ•••••• የሳይንሱ ቅልልቅ ተገግዳሮቶች ናቸዉ

4. የህዝብ ቁጥር በፍጥነት መጨመር
የሃገራችን የህዘብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ በመሄድ ላይ ነዉ፡፡ በአንፃሩ ደሞ የገብርናዉ ምርት ለሀገሪቱ ህዝበ ግጆታ በቂ ስላልሆነ መንግስት በየጊዜዉ ምግብ ከዉጭ ያስገባል፡፡ በገጠር ብቻም ሳይሆን በከተማም የምግበ ተረጂው ቁጥር ቸሁንም አልቀነሰም፡፡ ልምሳሌ በለገው አመት መንግስት ሰፊ የምግብ ዋስትናፕሮግራም ጀምሯል፡፡

ፕሮግራሙ ከዓለም ባንክ 300 ሚሊዮን ዶላር ብድር፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት 150 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በተመደበ በጀት የተጀመረ ነው፡፡ በፕሮግራሙ የታቀፉት 11 ከተሞች አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐዋሳ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ሰመራ፣ ሎጊያ፣ ጋምቤላና አሶሳ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየዉ ግበርናችን በዘመናዊ ሳይንስ አለመታገዙነ ነዉ ፡፡ ብዙዎች እነደሚስማሙበት ደሞ በራስ አቅመ የሚሰተራ የዘረ መል ምህንድስና ዋነኛዉና ዉጤታማዉ ነዉ፡፡

5. ልውጥ ህያዉነት በተፈጥሮም ሊከሰት መቻሉ
ልውጥ ህያዉነት በብዙ ቫይረሶችና በሌሎችም ህያዋን እንደምናየዉ ከሁኔታዎች ጋር እራስን ከማስማማት ጋር በተያያዘ ፣ ከጤና ችግር እና በሌሎችም ምክንያቶች ከሰዉ ጣልቃ ገብነት ዉጭ ያለ ዘረ መል ምህንድስና ሊከሰት ስለሚችል ሁለ ጊዜ የዘረ መል ምህንድስና ሳይንስ ብቻ ለተፈጥሮ መዛባት ተጠያቂ አድርጎ ማሰብ ተገቢ እይደለም፡፡

ህያዋን አንዳንድ ጊዜ ለአደገኛ ለጨረራዎች ሲጋለጡ ወይም ከተለያዩ ኬሚካሎች ጋር በራሳቸዉና ባጋጣሚ ሲገናኙ የዘረመል አቀማመጥ ለዉጥ ወይም ተፈጥሮዊ ልዉጥነት (spontaneous/natural mutation) ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህንንም ሁሌታ

6. የምርት ጥራት ፍላጎት
የዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ከተደረገ የግብርናን ምርትና ምርታማነት እንዲሀም ጥራትን ከማሳደግ ባለፈ የሰብሎች በሽታን የመቋቋም አቅምን እንደሚያጎለብት ግልፅ ነው። በአሁኑ ወቅት ለኢንዱስትሪ ግብዓት በሚሆኑ ተክሎች በዋነኛነትም በጥጥ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነዉ።
የአርሶ አደሮቻችንን ጉልበት ሊያግዙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማቅረብ እየተሰራም ይገኛል።

የብዝሀ ህይወት ህጉን ማሻሻል ያስፈለገበትም አንዱ ምክንያት የኢንዱስትሪውን ልማት ለመደገፍ ሲሆን በተለይ በማኑፋክቸሪንግ ንዑስ ዘርፍ ማነቆ ተደርጎ የሚጠቀሰውን የግብአት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

ለምሳሌ የጨርቃጨርቅ ንዑስ ዘርፍን ዋና ግብአት የሆነውን የጥጥ ምርት የሚታይበትን እጥረት በዘላቂንት ለመቅረፍ እንደ መፍትሔ የቀረበው ደግሞ ቢ.ቲ ኮቶን ተብሎ የሚታወቀውንና በዘረ መል ምህንድስና የሚመረተውን የጥጥ ምርት ለማስፋፋት ሲባል ነባሩን ህግ ማሻሻል ማስፈለጉ ይታወቃል፡፡

ባጠቃላይ በአንድ በኩል በፍጥነት እያደገ ያለ የህዝብ ቁጥር ያላትና በርካታ የልማት ፍላጎቶች በሁሉም ዘርፍ ማለትም በግብርና ፣ በኢንዱስትሪና በህክምና ዘርፎች እየመጡ ያሉባት ሀገራችን ኢትዮጵያ በሌላ በኩል በርካታ ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ የተለያዩ የትመህርት ተቋማትን በማስፋፋት ላይ ትገኛለች ። ይተቋማቱ ምስፋፋትም ሀገራችን በቂ የሰውና የቴክኖሎጂ አቅም እንዲኖራትና የዘረመል ምህንድስና ሳይንስን በብቃት እና የደህንነተ ህይወት መርሆዎች በተከተለ መልኩ እንድታጠናክር ይረዳታል።

ይህም በሌላ በኩል ደሞ የሌሎቸ የታላላቅ ሀገራት ታላላቅ ኩባንያዎች (Multinational Corporations) የራሳቸውን የዘረመል ምህንድስና ዉጤቶች ለኛ በማስለመድና ገበያችንን በመቆጣጠር ያመጡብናል ለሚለዉ ስጋትም በራስ አቅም በዚህ ሳይንስ በመጠቀም የራሳችንን የቴክኖሎጂ (የዘረመል) ዉጤቶች እንድናመርት ያስችላል። ስለዚህ ሳይንሱን በሩቁ ከመፍራትና ትክክነኛ ያልሆነ እስተሳሰቦችና ትርክቶች (Misconceptions and myth) ከማስፋፋትና ችግሮቹን ከማጋነን ይልቅ አስደናቂና ጥልቅ ከሆኑትን ከሳይንሱ ትሩፋቶች በተገቢዉ ለመጠቀም እንሞክር።

Related Post