አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ
የህዳሴው ግድብ እና አለም አቀፍ ህግ

በስንታየሁ ግርማ – የአሜሪካው ሁፐር ግድብ እ.ኤ.አ በ1929 እና በ1930ዎቹ በአሜሪካ ተከስቶ የነበረው የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት በአሜሪካ የተገነባ ግድብ ነው፡፡ ግድቡን ለመገንባት በ10 000ሰዎች የሚቆጠሩ አሜሪካኖች የተሳተፉ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰውተዋል ፡፡

ግድቡ ለኔቨድ ለአርዞንያን እና ለካርፎርኒያ ወዘተ ምእራብ ግዛቶች ዋነኛ የሀይል እና የብልፅግና ምንጭ ሲሆን በየዓመቱ በሚሊዬን የሚቆጠሩ ቱሪስቶች መነኽሪያ በመሆን በአሜሪካ ብልፅግናም ከፍተኛ አስተዋፆኦ አድርጓል፡፡ በተለይም ለምእራብ አሜሪካ ብልፅግና ቁልፍ ሚና አለው፡፡ ስያሜውን ያገኘው ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሐርፐርት ሁፐር ነው፡፡

ነፍሳቸዉን ይማርና ኢንጅነሪንግ ስመኘው በቀለ ለዋሽንግተን ፖስት በአንድ ወቅት እንደተናገሩት እንደሁፐር ግድብ ሁሉ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ኢትየጵያን ወደ ሥልጣኔ ማማ በመመለስ ታሪክ ይጻፍለታል ብለዋል፡፡ ኢጅነር ስመኝ እንደሚሉት ሁፐር ግድብ ለአሜሪካ ስኬት አሰተዋጽኦ ይኖረዋል ይላሉ፡፡ ምንም እንኳን ኢትዪጵያ ግድቡ ሁሉንም በፍትሀዊነት ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ብትገልፅም ግብፅ በተደጋጋሚ እና በተከታታይ እርስ በእርሱ የሚጋጩ መግለጫዎችን ስትሰጥ እና ድርጊቶችን ስታከናውን እየታየችው ነው ፡፡

ግብፅ ስለህዳሴው ግድብ መቆም የውጭ ቅዠታቸውን እያሰሙን ነው፡፡ ግብፅ የህዳሴው ግድብ እንደሚጠቅማት እና ጉልህ ጉዳት / No significant harm/እንደማያደርስ ብታውቅም የኢትዮያን እድገት እና ልማት በአዎንታዊ መልኩ ልታየው እና ልትቀበለው አትችልም የመጀመሪያው ምክንያት ለጥቁርህዝብ ለአፍሪካ ካላት ዝቅተኛ አመለካከት ይነሳል ፣

ሁለተኛ የኢትዪጵያ መልማት በአፍሪካ እና በአለም ተቀባይነቶን እሳደግ በመምጣት ቀጣይ አባይን የመጠቀም አቅሞ ያድጋልለሌሎች የተፋሰሱ ሀገሮች አይን ይገልጣል ዬህም ግብፅና ይጎዳል የሚል ከንቱ ስጋት አለባት፣

በሶስተኛ ደረጃ የግብፅ አብዮት መሰረታዊ እና መዋቅራዊ ችግሮች አሁንም አልትፈቱም። ችግሮቹ ተፈተዉ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እሲኪሰፍን ገዚወቹ አባይን የትኩረት ማስቀየሸ ያደርጉታል አንዳንድ ግብጻውያን የቅኝ ገዢ ውሎችን በመጥቀስ ናይልን የመጠቀም አለም አቀፍ መብት የእነሱ ብቻ እንደሆነ የሚገልፁ አሊ፡፡

የአባይ ወንዝን በተመለከተ የመጀመሪያው ስምምነት የተካሄደው እ.ኤ.አ. በ1891 ነበረ፡፡ በዚህ ስምምነት መሠረት ጣሊያን በአታባራ ወንዝ ላይ ግድብ ላለመስራት ከእንግሊዝ ጋር እንደተስማማች የሚያነሱ አሉ፡፡ ፕሮፌሰር አሊ አብደላ አል ግን በስምምነቱ በግል ቋንቋ ያልተቀመጠ ነው ይላሉ፡፡ፐሮፌሰር አሊ በሱዳን የኡምድሮማን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው፡፡

ሁለተኛው ስምምነት እ.ኤ.አ. ከ1902 በእንግሊዝ፣ ከጣሊያን እና በአፄ ሚኒሊክ የአባይን ወንዝ ላለማስቀረት እንደተስማሙ የሚያስቀምጡ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ስምምነቱ በወቅቱ በእንግሊዝ እና የዒትዮጵያ መንግሥት የዘውድ ም/ቤት ስላላፀደቁት ተቀባይነት የለውም የሚሉ አሉ፡፡ የእንግሊዝኛው እና የአማርኛው ፍቺዎች የተለያዩ በመሆናቸው ኢትዮጵያ እንዳላፀደቀችው ፕሮፌሰር አሊ ይናገራሉ፡፡

የ1929 እና የ1959 ስምምነት ለታሪካዊ መብት ዋነኛዋቹ መነሻዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ ስምምነቶች መሠረት፡-
– ግብፅ እና ሱዳን ጠብታ ውሃ ሳያስቀሩ ሙሉ በሙሉ በራሳቸው ተከፋፍለውታል፣
– ሌላ ይገባኛል የሚል ሀገር ከመጣ ከሁለት ሀገራት እኩል እንዲቀነስ ተስማምተዋል፣
– ግብፅ በናይል ወንዝ ላይ የሚጠራ ግድብ ድምፅ በድምፅ የመሻር መብት አጎናፅፏታል፣
– በሌሎች ሀገሮች በወንዙ ላይ የሚሠሩ ሥራዎች ለመከታተል የሚያስችል የቴክኒክ ቡድን ለማቋቋም ተስማምተዋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ሃሳቦች ከዓለም አቀፍ ሕግ እና ተቀባይነት ካለው መርህ አንፃር ማየቱ ተገቢ ነው፡፡

– በመጀመሪያ ደረጃ ግብፅ እና ሱዳን በ1929/በ1959 እኩል ተጠቃሚ ናቸው ብሎ በመውሰድ ተገቢ አይደለም፡፡
በ1929 ስምምነት ግብፅ ሱዳንን አላማከረችም፣፣ ምክንያቱም በወቅቱ ሱዳን የግብፅ አንድ የግዛት አካል ተደርጋ ስለምትወሰድ ነበር፡፡ በ1959 ስምምነት ደግሞ የሱዳን ውሃ ባለሙያዎች አስተያየት ግምት ውስጥ ሳይገባ የሱዳን ባለሥልጣናት ግብፅን በመፍራት እንደፈረሙት ፕሮፌሰር አሊ ታሪክን በመጥቀስ ይከራከራሉ፡፡ ከሁሉም በላይ በስምምነቱ የታችኛው የተፋሰስ ሃገራት በተለይም 86% የውሃ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ ሀሳቧ አልተካተተም፡፡ የስምምነቱም አካል አይደለችም፡፡ አንድ ስምምነት ተቀባይነት ያለው አለም አቀፍ ሕግ ሊሆን የሚችለው ስምምነቱን በፈረሙት እና ባፀደቁት አካላት መካከል ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎች የተፋሰስ ሀገራት በሁለት ስምምነቶች የመገዛት ግዴታ የለባቸውም፡፡

– ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት ተቀባይነት ያለው መርህ የእኩል ተጠቃሚነት እና ከፍተኛ ጉዳት ያለመድረስ መርሆዎች ናቸው፡፡ በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት የ1929 እና የ1959 ስምምነት የተፋሰሱ ሀገራት ዘጠኝን ያገላል፡፡ በመሆኑም ውሎቹ ከላይ የተጠቀሱትን መርሆዎች የሚጥሱ በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እና ጉዳይም ወደ ገላጋይ ጽ/ቤት ቢሄድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ስምምነቶቹ በይዞታቸው የእኩል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሳይሆን የሚያገሉ (Discriminatory) በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ሕግ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ለነገሩ ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት ለመላክም ኢትዮጵያ መስማማት ይኖርባታል፡፡

– እ.ኤ.አ. ሜይ 21/1997 የተመድ ለመጓጓዣነት የማይውሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም ባወጣው ኮንቬሽን መሠረት ሁሉም የተፋሰስ ሀገራት ወንዙን በሚጠቀሙበት ጊዜ የእኩል /ፍትሃዊ/ (Equality) አጠቃቀም መርህን በዋነኝነት መከተል እንዳለባቸው ያስቀምጣል፡፡
እኩል የመጠቀም መብት መርህ በተመለከተ አንዳንዶቹ በሁሉም ሀገራት እኩል ማከፋፈል ነው በማለት ይተረጉሙታል፡፡ ይህ ግን በአብዛኛው ተቀባይነት የለውም፡፡ በኮንቬሽኑ መሠረት የእኩል /ፍትሃዊ ሚዛናዊ መርህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚይዝ ነው/ በአንቀጽ 6 መሠረት/
1. የጂኦግራፊ፣ የሃይድሮ ግራፊክ፣ የሃይድሮሎጂክ፣ የኦኮሎጂካል እና ሌሎች የተፈጥሮ ሁኔታ መመዘኛዎች፣
2. በተፋሰስ የሚገኝ ሀገራት ያለው የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች፣
3. አንድ ሀገር ውሃውን ሲጠቀም በሌላኛው ተፋሰስ ሀገር ላይ ያለው ተፅዕኖ፣
4. በጥቅም ላይ ያለ እና እም ቅ የውሃ አቅም፣
5. ውሃውን ለመጠበቅ፣ ለመከላከል፣ ለመበልፀግ ያለው ጠቀሜታ እና ለዚህ የሚውለው ወጪ፣
6. አማራጭ የውሃ ምንጮች

በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት ሀገራት መከፋፈል እንዳለባቸው ኮንቬሽኑ ያስቀምጣል ፡፡ በእነዚህ መመዘኛዎች መሠረት ያልተከፋፈለ ድንበር ተሻጋሪ ወንዝ አጠቃቀም በድርጅቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ለእነዚህ መመዘኛዎች ቀረቤታ ያለው የቅኝ ግዛት ውሎች ሳይሆኑ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት /የኢንተሺ ስምምነት/ ነው፡፡

ስለዚህ ለግብፅ እና ሱዳን በዘላቂነት የሚያወጣቸው የትበብር ማዕቀፍ ስምምነት መሠረት መፈረም ነው፡፡ ለነገሩ ስምምነቱ ከአባል ሀገራት 2/3ኛው ካፀደቁት ዓለም አቀፉ ተቀባይነት እና አስገዳጅነት ያለው ሕግ ይሆናል፡፡ እስካሁን ስምምነቱን ኢትዮጵያ አፅድቃዋለች፡፡ በቀጣይም ዩጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ኬንያ፣ታንዛንያ እና ሱዳን ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም ናይልን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሕግ ይሆናል፡፡

በ1997ቱ የተመድ ኮንቬሽን መሠረት ከእኩል ተጠቃሚነት በተጨማሪ ጉዳት ያለማድረስ መርህ ሌላኛው መመዘኛ ነው፡፡ የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ በግብፅ ላይ ትርጉም ያለው ጉዳት እንደማይደርስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ አስቀምጣለች፡፡ እንዳውም የግድቡ ሥራ ሲጀመር ታላቁ መሪ ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፍትሃዊ አጠቃቀም የሰፈነ ቢሆን ኖሮ የግድቡን ወጪ ሥራን 20 በመቶ ሱዳን 30 በመቶ ግብፅ ሊሸፈኑ ይገባ ነበር፡፡ ባለሙያዎች እንደሚገልፁት በኢትዮጵያ የሚሠራ ግድብ ትነትን
በመቀነስ ተጨማሪ ውሃ ያስገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የሚሠራ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ የታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ከጎርፍ እና በደለል ከመሞላት ይከላከላል፡፡ የተመጠነ የውሃ ፍሰት ዓመቱን ሙሉ እንዲኖር ያስችላል፡፡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሃይል አቅርቦት እንዲኖር ያስችላል ይላሉ አንዳንድ የዘርፉ ባለሙያዎች ምክራቸውን ሲለግሱ ዘላቂው ስትራቴጂ የአባይን ወንዝ በዘላቂነት ለመጠቀም ውሃው የሚከማችበትን እና አስዋን ግድብ ከፍተኛ ትነት ካለበት ግበፅ እና ሱዳን ይልቅ ወደ ቀዝቃዛም የኢትዮጵያ ክፍል ማሸጋገር ነው ይላሉ፡፡

አንዳንድ ግብፃዊያን ሌላኛው የሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ 55.5 ቢሊዮን ኪቢዩክ ሊትር ውሃ የመጠቀም ታሪካዊ መብት አለኝ፡፡ ይህም ተለምዷዊ አለም አቀፍ ሕግ ሆኗል የሚል ነው፡፡ እንደ ልምድ ተቀባይነት ያለው ተለምዷዊ አለም አቀፍ ሕግ ተቀባይነት የሚኖረው ተቃዋሚ ወገን ባይኖር ሲቀር ነዉ፡፡ ይሁንና ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የመጠቀም መብት እንዳላት ለግብጽ እና ለሌሎችም በየጊዜው ከማሳወቋም በላይ ቅኝ ገዢዎች እና ግብጽ ኢትዮጵያን በማግለል የተዋዋሉትን ስምምነቶች በተደጋጋሚ ለሀገሪቱ እና ለዓለም አቀፍ ተቋማት ሊሊጎ ኦፍኔሽን እና ለተመድ በፅሁፍ መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

በተለይ አጼ ሚኒሊክ እና አጼ ኃይለሥላሴ ተቃውሟቸው በፅሁፍ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ታሪካዊ መብት የሚባለውን ኢትዮጵያ ተቃውሞዋን የገለፀችበት ስለሆነ በዓለም አቀፍ ሕግ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም በ1978 በቪየና በፀደቀው ኮንቬሽን መሠረት ሀገራት ከቅኝ ግዛት ሲላቀቁ መውረስ ያለባቸው ድንበር እንጂ ሌሎች መብቶችን እና ግዴታዎችን እንዳልሆነ ያስቀምጣል፡፡ ቅኝ ገዢዎች ውል /ስምምነት/ በየጊዜው ካለው የሰው ልጅ ፍላጎቶች ጋር የሚያያዙ እና የሚሻሻሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ውል ሳይሆን መቅደም ያለበት የሰው ልጅ ፍላጎት ነው፡፡ በ1920ዎቹ እና በ1950ዎቹ ያሉ የሰው ልጅ ፍላጎት ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር አንድ እና ያው ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ ፍላጎት ጋር ውሳኔዎች በየጊዜው እየተሻሻሉ መምጣት ይገባቸዋል፡፡ በቅኝ ገዢዎች አማካኝነት የተገቡትን ስምምነቶች የማክበር ግዴታ የላባቸውም፣፣ በግዴታ የነፁ ሀገራት መሆን እንዳለባቸው ኮንቬንሽኑ ይደነግጋል፡፡

ሲጠቃለል የአባይን ወንዝ በተመለከተ ለኤሌክትሪክም ሆነ ለሌላ አገልግሎት የሚውል አለም አቀፍ ሕግ ኢትዮጵያን የሚደግፍ እንጂ የሚከላከል አይደለም፡፡

Related Post