አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

አስገራሚው የፀሃይ ክስተት

አስገራሚው የፀሃይ ክስተት
አስገራሚው የፀሃይ ክስተት

በአብይ ደምለው – በተለይ ባለፉት አራት አመታት በሰማያቱ ላይ እየተከሰቱ ያለፉ “ክስተቶችን” በተራ ትዕይንትነት እያለፍናቸው የፈጣሪን “መልዕክቶች” ልብ ሳንላቸው የቀረን ይመስለኛል።

በ50ና በ100 አመታት እንኳን ተከስተው ያላየናቸው ኩነቶች በዚህች አራት አመታት ተደጋግመው ሲከሰቱ አይተናል።
1. የዛሬ 3 አመት መቀሌ፣ ጎንደርና ባህር ዳር ሰማዮች ላይ የተከሰተው ቢጫ አሸዋ፣
2. የዛሬ 3/4 አመት የሰሜኑን የአገራችንን ሰማያትንና ሰብሉን የወረረና ያወደመው የአንበጣ መንጋ፣
3. ጂጂጋ ላይ የዘነበው ጥቁር (ጥላሸት) ዝናብ፣
4. በትላንትናው ዕለት ከመቀሌ አስከ አዲስ አበባ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሀረርና ድሬዳዋ፣ ከድሬዳዋ እስከ ጅቡቲ ሰማያት ላይ የታየው የፀሀይ ልዩ ትዕይንት ወዘተ

በተለይም የትላንትናው ልዩ ክስተት ብዙዎችን ያነጋገረና በብዙ ቦታዎች ላይ በቀስተደመና ህብረ ቀለማት ጭምር የታጀበ (Colorful) ነበር።
የዚህ ክስተት ትርጓሜ በስነፈለግ (Astronomy & Cosmology) ባለሙያዎች ምን እንደሚባል ለመስማት ጓጉተናል።
በዚያው ልክ ደግሞ መንፈሳዊ አባቶች ምን ትርጉም ሊሰጡት እንደሚችሉ የእነርሱንም ትንታኔ እየጠበቅን ነው።

ይሁንና ከእስከዛሬ የኮስሞ ልዩ ክስተቶች በመነሳት በጣም ከበድ ያለ መልዕክት እንደተላለፈ ግን እርግጠኛ መሆን ይቻላል።
በግሌ በትላንትናው ዕለት ለማነጋገር የሞከርኳቸው የተለያዩ ዕምነት ተቋማት አባቶች “የአገርና ህዝብ መከራ የማብቂያ ልዩ የሰላም ምልክት” እንደሆነ ነግረውኛል።
በትንሽ ትልቁ መደናቆር፣ መናቆር እና መገዳደልን አቁመን ለሠላም ዕድል እስከሰጠን ድረስ መጪው ዘመን ጥሩና ሰላማዊ ይሆናል ብለውናል።
አሜን! ፈጣሪ ይህንን ዘመን ያምጣልን!

እስቲ እናንተም ከእናቶችና ከአባቶች ዕውቀት የተሰጡ ትርጓሜዎች ካሉ ጨምሩባቸው።

Related Post