አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

አርሂቡ ቻይና

አርሂቡ ቻይና
አርሂቡ ቻይና

በስንታየሁ ግርማ – መረጃዎች እንደሚሳዩት የቻይና አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት 16.94 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከአለም ኢኮኖሚ 18 በመቶ ይሸፍናል፡፡ ለአለም ኢኮኖሚ እድገትም 40 በመቶ በመሠሸፈን የመጀመሬያዊን ደረጃ ይይዛል፤፤

የአሜሪካ የግብርና መምሪያ በበኩሉ የቻይና በ2020/2021 የቡና ፌጆታ ከባለፍዉ አመት ጋር ሲነፃፀር 80 በመቶ በማደጉ ምን ያሕል መልካም እድል እንዳለ ያሣያል፡ ቡና ኢትዮጵያ ለአለም ያስተዋወቀችው ምርጥ ስጦታ ነው፡፡ ቡና የኢትዮጵያ ብራንድ ነው፡፡ ከቡና የተሻለ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቅ ምርትና አገልግሎት ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ቡና ኢትዮጵያውያንን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ የሚያስተሳስር ማህበራዊ ካፒታል ነው፡፡ ማህበራዊ ካፒታል ለሃገር ብልፅግና ዴሞክራሲ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

የማህበራዊ ካፒታል መበልፀግ በበኩሉ ለሃገር ብልፅግና ተመልሶ ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል፡፡ በዚህ ውድድር በበዛበት የሉአላዊነት ዘመን ሃገራት አንፃራዊ ብልጫቸውን በመለየት ምርትን (አገልግሎትን) ብራንድ በማድረግ ዜጎች ብራንዳቸውን ለማስተዋወቅ እንደ አንድ ሰራዊት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ከቡና የተሻለ ምርት ወይንም አገልግሎት የለም፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቡና ከነዳጅ ቀጥሎ ከፍተኛ ግብይት የሚካሄድበት ሸቀጥ ነው፡፡ በየቀኑ ከ3 ቢሊዮን ስኒ በላይ ቡና በአለም ይጠጣል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና በአለም ተወዳዳሪ ቀርቶ አጠገቧ የሚደርስ ቡና የሚያቀርብ ሃገር የለም፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ. በ2014 ታዋቂ የሆኑ የቡና ኤክስፖርተሮች ተጠይቀው ለኢትዮጵያ ቡና 25 ነጥቦች በመስጠት በአንደኛ ደረጃ ሲያስቀምጡት ኬንያ በግማሽ አንሳበ 12 ነጥቦች 2ኛ ደረጃ ኮሎምቢያ በ10 ነጥቦች 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና በአለም በተዛባው የንግድ ስርዓት ምክንያት ኢትዮጵያ ከቡና መጠቀም የሚገባትን ያህል ተጠቅማለች ማለት አይቻልም፡፡ ለዚህ ደግሞ ከመፍትሄዎች መካከል በፍጥነት በማደግ ላይ ባሉት ሃገሮች በተለይም በወጣቶች ላይ አተኩሮ የኢትዮጵያን ቡና የማስተዋወቅ ስራ ጀምሮ አጠናክሮ እና በድግግሞሽ ማስቀጠል ነው፡፡

መረጃወች እንደሚሳ ዩት የቻይና አጠቃላይ ብሄራዊ ምርት 16.94 ትሪሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከአለም ኢኮኖሚ 18 በመቶ ይሸፍናል፡፡ ለአለም ኢኮኖሚ እድገትም 40 በመቶ በመሠሸፈን የመጀመሬያዊን ደረጃ ይይዛል፤፤(ሹንዋ፣2022)፤፤ ዘኢኮኖሚስት እንደዘገበው ቻይና የሻይ ተጠቃሚ ሃገር ብትሆንም አሁን ቡና በመልመድ ላይ ነው ይላል፡፡

ይሁንና ዘኢኮኖሚስት ወጣት ቻይናውያን ቡና ከሚጠጡ በላይ በቡና መሸጫ ሱቆችም ምስል መለዋወጥ አመቺ ሆኖ አግኝተውታል ይላል፡፡ ዘኢኮኖሚስት እንደሚለው የደቡብ ምእራብ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ በሆነችው ቹንዱ ሃንግሻይ የቡና መጠጥ አሰራርን ስትሞክር አግኝተናታል፡፡ ትምህርት የሚሰጠው ቡና ከሚቆላበት እስከ ቡና ጠጪዎች መስተንግዶ ክህሎትን የያዘ ነው፡፡

ከአውሮፓ ላኪ ማእከላት ስለ ክህሎቱ ማረጋገጫ አግኝታለች፡፡ በ20ዎቹና በ30ዎቹ የሚገኙ 7 ሴቶች የቡና መጠጥ መሸጫ ሱቅ ለመክፈት ሃሳብ ያላቸው ትምህርቱን እየተከታተሉ ነው፡፡የአሜሪካ የግብርና መምሪያ በበኩሉ የቻይና በ2020/2021 የቡና ፌጆታ ከባለፍዉ አመት ጋር ሲነፃፀር 80 በመቶ በማደጉ ምን ያሕል መልካም እድል እንዳለ ያሣያል፡፡ቡና የሰለጠነ ሰዉ እና ሃገር መጠጥ በለዉ የተናገሩት የቶማስ ጀፈርሰን ንግግር በቻያና በመካከለኛእና ከፍተኛ ከተሞች የወጣቶች የቡና ተጠቃሚነት መጨመር የአባባሉን እዉነተኛነት እያረጋገጠ ነዉ

እስከ 1990ዎቹ (እ.ኤ.አ.) ድረስ ቡና በቻይና የሚጠቀሙት የውጪ ሃገር ዜጎች ብቻ ነበሩ፡፡ ያውም ማግኘት የሚቻለው በቅንጡ ሆቴሎች ብቻ ነበር፡፡ ሁኔታዎች መሻሻል ያሳዩት ለስታር ባክስ በ1999 እ.ኤ.አ. በቻይና የቡና ሱቅ ሲከፍት ነው፡፡ ስታር ባክስ ቡናን ለማለማመድ ወተት እና ስኳር ቀላቅሎ በመሸጥ ነበር የጀመረው፡፡ ይሁንና እንደየ አለም የቡና ድርጅት መረጃ መሰረት አሁንም ቢሆን በቻይና አማካይ የቡና ፍጆታ መጠን በአመት ለአንድ ሰው አምስት ስኒዎች ብቻ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአሜሪካ ወይንም በጃፓን ቡና ከሚጠቀመው ሰው አንድ ሶስተኛ ብቻ ነው፡፡

ይሁንና በመካከለኛ ገቢ ባላቸው ቻይናዎች ቡና መጠጣት ፋሽን እየሆነ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ስታርባክስ 3,800 የቡና መሸጫ መዳረሻዎች በቻይና አሉት፡፡ ይህ ደግሞ ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያደርጋታል፡፡ ስታቲስትዩ የተባለ የቢዝነስ ኢንተሊጀንስ ተቋም እንደሚለው ከሆነ የተቆላ ቡና ገበያ በቻይና በየአመቱ አስር በመቶ እያደገ ነው፡፡

አሁን ግን ላክንኮፊ ቤጂንግን መሰረት አድርጎ ተመስርቷል፡፡ ከተቋቋመበት ከዛሬ ሁለት አመት ጀምሮ እስካሁን 2,300 መዳረሻዎችን ከፍቷል፡፡ ሜይ 17, 2019 በወጣው የስቶኩ የጨረታ ገበያ 570 ሚሊዮን ብር ሰብስባ ዋጋውን ወ 4 ቢሊዮን ዶላር አሳድጓል፡፡ የላኪን አስገራሚ እድገት በቻይና የለውጥ ንፋስ እየነፈሰ መሆኑን ማሳያ ነው፡፡

ከእንግዲህ ቻይናውያን ቡናን እንደቅንጦት አያዩትም፡፡ ብዙዎቹ የላኪን ቡና መሸጫ ሱቆች ተጠቃሚዎች በአእምሮ ስራ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍል ናቸው፡፡ በጣም የስራ ጫና ያለባቸው በመሆኑ ትእዛዝ የሚሰጡት በኦንላይን ነው፡፡ የሻይ እና የቡና ገበያ በቻይና የተለያዩ ናቸው፡፡ የሻይ ቤቶች ከ40 ዓመት በላይ ቻይናውያን ይዘወተራሉ፡፡ በቡና መሸጫ ሱቆች ግን ከ40 ዓመት በላይ ያሉ ቻይናውያን እምብዛም አይገኙም፡፡ ወጣት ቻይናውያን የቡና መሸጫ ሱዎችን የሚጠቀሙባቸው ለማህበራዊ ትስስር ነው፡፡ ብዙዎቹ ቡና እየጠጡ ምስላቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ይለቃሉ፡፡

ከዘኢኮኖሚስት ዘገባ መረዳት እንደምንችለው በቻይና ገበያ ሰብሮ ለመግባት ብዙ እድሎች እንዳሉ የቡና ጠቀሜታን የሚያስረዱ ስነምግባርን የተከተሉ ማስታወቂያዎችንና የፕሮሞሽን ስራዎች መስራት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ ጥናቶች እንደሚያስረዱት ቡና መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 ዓመታት እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡

የእድሜ ጣሪያ ደግሞ የፍትሃዊ ሃብት ክፍፍል መግለጫዎች አንዱ ከሆነው የሰው ሃብት ልማት (human development index) አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ ቻይናውያን ቡናን በመጠጣት የሚያገኙትን ጥቅም (call to benefit) መሰረት ያደረገ መልእክት ቀርፀን ለቻይናውያን በማስተላለፍ ወደ ቻይና ገበያ ሰብረን መግባት ለነገ የማይባል ስራ ነው፡፡ አርሂቡ ቻይና!

Related Post