አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

አሪሂቡ አፍሪካ – የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል

አሪሂቡ አፍሪካ - የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል
አሪሂቡ አፍሪካ - የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል

በስንታየሁ ግርማ አይታገድ – ከቅርብ አመታት ወዲህ የቡና ባህል በአፍሪካ እያደገ ነው፡፡ ምንም እንኳ አፍሪካ ለአለም ከሚቀርበው 13 በመቶ ብታበረክትም እና የቡና መገኛ አህጉር ብትሆንም ከሌላው ዓለም ጋር ሲወዳደር የአፍሪካውያን ቡና የመጠጣት ባህል የተፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያ በስተቀር፡፡ አፍሪካውያን ከሚያመርቱት ምርት አብዛናውን ለአለም ገበያ የምታቀርብ ፍጆታዋ በጣም ትንሽ ነበር፡፡ አሁን ግን በመጠኑም ቢሆን ሁኔታዎች እየተለወጡ ነው፡፡

የአፍሪካ መንግስታት የሀገር ውስጥ የቡና ፍጆታን እያበረታቱ ነው፡፡ ለምሳሌ ካሜሩን «የቡና ፌስቲቫል» የሚል ሁነት በማዘጋጀት በሁሉም የመንግስት መ/ቤቶች ቡና መጠጣትን እያስተዋወቀች ነው፡፡ በደቡብ አፍሪካም ከፋስት ፉዱ እና ወደ ቤት ተወስደው ከሚጠቀሙበት መጠጦች ውስጥ በየአመቱ በአማካይ 2.8ቱ የቡና ሱቆች ይሸፍናሉ፡፡ የቡና ኢንዱስትሪውም በአመት በአማካይ በ7.1 በመቶ እያደገ ነው፡፡ የቡና መጠጣት አብዮት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ነው ይላሉ ተንታኞች፡፡

በናይጄሪያም ውስጥ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍል እያደገ በመምጣቱ እ.ኤ.አ በ2010 እና 2015 በናይጄሪያ ቡና መጠጣት 20 በመቶ እያደገ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ በ2020 ናይጄሪያውያን 1000 ቶን ቡና ይጠጣሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንን ፍጆታ ደግሞ የናይጄሪያ የቡና ምርት አይሸፍንም፡፡ ይህንን እድል ኢትዮጵያ ልትጠቀምበት ትችላለች፡፡ የአሜሪካ የግብርና ምርት መምሪያ እንደገመተው ኢትዮጵያ በ2022 /2023 በኢትዮጵያ 495ሺህ ሜትሪክ ቡና በማምረት ሪከርድ የሆነ ምርት በማምረት ኤክስፖርቱም ሪከርድ እንደሚሆን ተንብይዋል፡፡

ከአፍሪካ አብዛኛው የሮብስታ ቡና አምራች አገራት የሆነችውም ዩጋንዳ የአገር ውስጥ ፍጆታዋን በ20 በመቶ በአማካይ በማሳደግ ኢኮኖሚዋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ትችላለች፡፡ ዩጋንዳም የቡና ባለስልጣን የሀገር ውስጥ ፍጆታን ለማበረታታት ንቅናቄ ጀምሯል፡፡ ይህም በሳምንት ውስጥ 20ሺህ ስኒቡና በነጻ ማቅረብ ያካትታል፡፡

በጎረቤታችን ኬንያም መካከለኛው ህብረተሰብ እያደገ በመምጣቱ የኬንያውያን ቡና የመጠጣት ባህል ለማሳደግ እና ከሻይ ይልቅ ቡናን እንዲጠጡ ለማበረታታት የቡና ሱቆች በማስፋፋትና በማበረታታት የሸማቹን እምነት ለማሳደግ እየጣረች ነው፡፡

ይሁንና እነዚህ ጥረቶች ሁሉ በቂ ሆነው አልተገኙም፡፡ ከዚህ በመነሳት ከዳበረው የኢትዮጵያ ቡና የመጠጣት ባህል ልምድ ለመውሰድ አፍሪካውያን ከኢትዮጵያ የቡና ባህል ልምድ በመቅሰም እና ወደ ራሳቸው ለመውሰድ በአዲስ አበባ መክረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የቡና መገና አገር ብቻ ሳትሆን ለዘመኑ የዳበረ የቡና ባህል ያላት አገር በመሆኗ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኢትዮጵያ በአማካይ ከምታመርተው የቡና ምርት ከግማሽ በላይ ለአገር ውስጥ ፍጆታ ታውለዋለች፡፡ ይህ ልምድ የኢትዮጵያን ቡና ቀጣይነት ከማረጋገጥ አኳያ መልካም እድል ነው፡፡

በአፍሪካ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ቡና የመጠጣት ባህል በተለይም በመጠኑ እየጨመረ ነው፡፡ በከተሞች የቡና ሱቆች እየተስፋፉ ነው፡፡ የመካከለኛው ህብረተሰብ ክፍልም እያደገ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ቡና ኤክስፖረት ማደግ ከፍተኛ እድል ነው፡፡ የአለም የቡና ገበያ ዋጋ ወሰኖች ባደጉ አገሮች ትንሽ ቡና ቆዪዎች እና ድንበር ተሸጋሪ ኮርፖሬሽን ናቸው፡፡ ዋጋውን የሚወስኑት እነሱ በመሆናቸው የአለም አነስተና ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች ገቢ የምርት ወጪውን እንኳን የሚሸፍን አይደለም፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያን ቡና ይህንን ስጋት የመቋቋም እድሎች አሉት፡፡
እነሱም፤
1. ኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው ልዩ ቡና / Speciality Coffeee ባለቤት በመሆኗ 2/3ናውን ኢትዮጵያ ቡና ልዩ ቡና ተብሎ የመመደብ ብቃት አለው፡፡ ሸማቾች ደግሞ ለልዩ ቡና የተሸለ ክፍያ የመክፈል ልምድ እያዳበሩ ነው፡፡

2. የኢትዮጵያ ቡና ከ90 በመቶ በላይ ኦርጋኒክ ተብሎ የሚፈረጅ መሆኑ ከሸማቾች ጠንነት ጋር ተያይዞ ተቸማሪ እየሆነ መምጣቱ እና የተሸለ ክፍያ እያደገ መምጣቱ፤

3. « ፍትሀዊ ንግድ » የሚደረግ ንቅናቄ እያደገ መምጣቱ የቡና ቀጣይነት በአለም በተዛባው የንግድ ስርዓት ምክንያት አነስተኛ ቡና አብቃይ አርሶ አደሮች እየተጎዱ በመሆኑ ፍትሀዊ ንግድ ንቅናቄ አቀንቃኞች አነስተኛ አምራች አ/አደሮች የምርት ወጪያቸውን ለመሸፈን የሚያስችል እና ኑሯቸውን ለመግፋት የሚያስችል ሲስተም እንዲኖር አየጣሩ ነው፡፡ በሸማቹም ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፤ ቡና ጠጪዎች ቡናው የት እንደተመረተ፣ እንዴት እንደተዘጋጀ እና እንደታሸገ በማወቅ የተሻለ ዋጋ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፡

ከቡና ምርት ጀርባ ያለው አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና የአካባቢ ጉዳዮችን ቡና ጠጪዎች በማወቅ የተሻለ ክፍያ ለመክፈል ፍላጎት እያሳዩ ነው፡፤ በድርጊትም እየገለጹ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ ይህንን ስለምታሟላ ለአ/አደሮቻቸው ምርጥ እድል ነው፡፡ ለዚህም ነው የሚቀጥለው አመት የቡና ጣዕም ውድድር ሀገራችን የምታስተናግደው፡፤

4. የአፍሪካ ኢኮኖሚ ማደግ በአለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት አገሮች አብዛኛዎቹ ከአፍሪካ ናቸው፡፡ በአፍሪካ ወጣቱ እና መካከለኛው የህብረተሰብ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ ቡና መጠጣት በአሁኑ ሰዓት የሞደርናይዜሽንና ስልጣኔ ምልክት እየሆነ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን ከሁለት ስኒ ቡና በላይ መጠጣት የእድሜ ጣሪያን በ15 አመታት እንደሚጨምር ተረጋግጧል፡፡ ጬእድሜ ጣሪያ ደግሞ ከፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል (HDI) አንዱ ነው፡፡ እያደገ የሚመጣውን የአፍሪካ ቡና ፍጆታ ደግሞ ሊሸፍን የሚችለው የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው የኢትዮጵያ ቡና ምርት ነው፡፤ ስለዚህ ፊታችንን ወደ አፍሪካ ማዞር አለብን፡፡

5. የኢትዮጵያ ቡና መገና አገር በመሆኗ ጥሩ ገጽታ እና መልካም ስም አዳብሯል፡፡ ሸማቾች ደግሞ ከምርቱ በላይ ዋጋ የሚከፍሉት ለመልካም ስም ነው፡፡ስለዚህ የአፍሪካን ወጣት የበለጠ ቡና መጠጣት በማስተዋወቅ ለመሳሌ ከፕርሚርይር ሊግ ከለቦች አንዱን ስፖነሰር በማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡

Related Post