አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ተጎጂው ሸማቹ እንጂ ባለሱቁም ሆነ ተመላላሽ ነጋዴው አይደለም

ተጎጂው ሸማቹ እንጂ ባለሱቁም ሆነ ተመላላሽ ነጋዴው አይደለም
ተጎጂው ሸማቹ እንጂ ባለሱቁም ሆነ ተመላላሽ ነጋዴው አይደለም

በመላኩ ብርሃኑ – የገንዘብ ሚኒስቴር ማንኛውም ሰው ከውጭ ሃገር በሻንጣ ይዞት በሚገባው እቃ ላይ ጥብቅ የሆነ ረቂቅ መመሪያ አጽድቆ ተግባራዊ ለማድረግ ተዘጋጅቷል። በዚህ ረቂቅ መመሪያ መሰረት ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የሚፈቀድላቸው የግል መገልገያ የቁሳቁስ ዓይነቶች ቀድሞ ከነበሩበት 130 ወደ 16 አይነት ብቻ ወርደዋል።

ለግል አገልግሎት የሚውሉ ብዛታቸው ከአንድ አይነት ያልበለጠ አልባሳት እና ጥቂት ጥቃቅን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብቻ ናቸው የተፈቀዱት። በርግጥ ነጋዴ ፍቃድ አውጥቶና ግብር ከፍሎ እየሰራ ተመላላሾች ግን የቀድሞውን መመሪያ ለንግድ እና ለማይገባ ብልጽግና ተጠቅመውበታል።ሁሌም ሰው ፍቃድ ሲሰጠው ቀዳዳ ማስፋቱ የሚወገዝ ተግባር ነው።

ነገር ግን ተመላላሽ ነጋዴን ወደዚህ ተግባር የመራው በየሄደበት ገዢ በማግኘቱ ነው።ሸማቹ የቤት ኪራይ የሚያስከፍሉትን ነጋዴዎች ዋጋ መቋቋም ስለሚያቅተው ቀነስ ያለለትን ይሸምታል። ሸማቹን ወደዚህ መንገድ የመሩት ደግሞ በኔ አተያይ ራሳቸው ነጋዴዎች ናቸው።

የሃገር ውስጡ የሞል እና ሱቆች የሸቀጥ ገበያ ከአንድ እቃ ላይ 500 ፐርሰንት ማትረፍ ላይ ያነጣጠረ የነጋዴ ዘረፋ ነው።3 ሺህ ብር በማይሞላ ገንዘብ የገዛውን ጫማ 11ሺህ ብር ዋጋ ለጥፎ የሚሸጥ የሚለጥፍ ነጋዴ ነው በየሞሉና በየቡቲኩ ያለው።ይህ ሃሰት አይደለም።

እንግዲህ መመሪያው ተግባራዊ ሲሆን ወደሃገር ውስጥ የሚገባ እቃ ከፍተኛ ገደብ ስለሚጣልበት የአልባሳት እና መዋቢያዎች ዋጋ አሁን ካለበት የት እንደሚደርስ መገመት ቀላል ነው። ያኔ ደግሞ በግላጭ ያገኘውን ሸማች በኮንቴይነር የሚያመጣው ነጋዴ ጥሩ አድርጎ ያደቅቀዋል። በመሃል ተጎጂው ሸማቹ እንጂ ባለሱቁም ሆነ ተመላላሽ ነጋዴው አይድለም። ለዚህ ነው ጠንካራ የኮንሲውመር አሶሲዬሽን (የቀበሌው ሸማቾች አይነት አይደለም) የግድ የሚጭያስፈልገው!!

Related Post