አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ብራንድ የሚሰርቁ በሞት ቢቀጡስ?

ብራንድ የሚሰርቁ በሞት ቢቀጡስ
ብራንድ የሚሰርቁ በሞት ቢቀጡስ

በስንታየሁ ግርማ – በሙስና እና በመግደል መካከል ያለዉ ልዩነት ኢምንት ስለመሆኑ የሚናገሩ ምሁራን ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። የተደራጀ ሙስናና የሠብአዊ መብቶች ጥሰት እ.አ.አ. በ2ዐ15 በኢትዮጵያ የደረሰውን ቀውስ አስከትሏል /ክሪያ 2ዐ19/

ክሪያ አክላም ሙስና በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ገፅታ ተላብሶ የተንሠራፋ እንደሆነ ትገልፃለች፡፡ ኪራይ ሠብሣቢነት እና የመንግሥት ሥልጣን መፈናጠጥ ዋና መገለጫዎቹ እንደሆኑ ክሪያ በፅሁፏ አስቀምጣለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድም የሀገሪቱን ህልውና እየተፈታተነ ስለሆነ ሙስናን መዋጋት ቁልፍ
ተግባራቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አይፈራም ባየህ እና ሙጨበ 2ዐ15 ፤ተሾመ በ2ዐ16 በጥናታቸው ሙስና የሀገሪቱን እድገትና ልማት እያቀጨጨው መሆኑን ጠቅሰው ለሙስና መስፋፋት ዋነኛ ምክንያቶች ብለው ከዚህ የሚከተሉትን ነጥቦች አስቀምጠዋል፡፡
 የተጠያቂነት እና የአሠራር ግልፅኝነት አለመኖር
 ዝቅተኛ የዲሞክራሲ ባህል እና ልምድ
 ግልፅኝነት የጐደላቸው ህጐች እና አሠራሮች (አምባገነንነት)፣
 ዝቅተኛ የተቋማት ቁጥጥር
 አስተማሪ ቅጣት አለመኖር
 ከመጠን በላይ የተማከለ ሥልጣን እና ሀብት

እንደ አሜሪካ መንግስት አቋም ሙስና ህገ-ወጥ በሆነ መልኩ የሚከናወኑ የገንዘብ፣ የጦር መሣሪያ፣ የመድሃኒት፣ የአደንዛዥ ዕፅ እና የሰዎች ዝውውርን፣ የግብር ስወራንና ማጭበርበር የሚያካትት መሆኑን ገልጾ ድርጊቶቹ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ስጋት መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

ትራንስፖረንሲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከተንሰራፋባቸው አገራት መረጃ መሠረት ኢትዮጵያ ከ18ዐ ሀገሮች ውስጥ 1ዐ6 ሀገሮችን በመብለጥ በ1ዐ7ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ይህ መረጃ ሙስና በኢትዮጵያ ምን ያህል አሣሣቢ ደረጃ ላይ እንዳለማሣያ ነው፡፡ የአለም ባንክ በሚያወጣው የአስተዳደር ጥራት መለኪያዎችም ኢትዮጵያ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እ.ኤ.አ. በ2ዐ17 ባንኩ ባወጣው የኢትዮጵያ አፈፃፀም /ከመቶኛ/ እንደሚከተለው ነው፡፡

 ሙስናን በመቆጣጠር 33.2
 የመንግሥት አሠራር ቀልጣፋነት 23.6
 በፖለቲካ መረጋጋት 7.6
 የተቆጣጣሪ አካላት ጥራት 13.9
 በህግ የላይነት 33.7
 በተጠያቂነት 9.9

በቀውስጥ መመዘኛ መሠረት ደግሞ ትሬስ የተባለው ድርጅት የኢትዮጵያን የቀውስ ደረጃ ከ2ዐዐ ሀገሮች 178ኛ በማስቀመጥ ለቀውስ በከፍተኛ ሁኔታ ከተጋለጡ ሀገሮች ተርታ ያሳልፈታል፡፡

ለንግድ ሥራ አመችነትም ከ19ዐ ሀገሮች 161ኛ በመቀመጥ ከኢትዮጵያ ይልቅ 16ዐ ሀገሮች ለንግድ ሥራ አመቺ ሆነዋል፡፡ ይህ ደግሞ ዛሬ ለሉላዊነት ዘመን በውድድር ማሸነፍ እና መሸነፍ የሀገርሉ ዕላዊነት የማስቀጠል ጉዳይ በመሆኑ እንደ ሀገር ምን ያህል አደጋ ላይ መሆናችንን ማየት ይቻላል፡፡

ከላይ ለተጠቀሱት አለም አቀፍ መመዘኛዎች አነስተኛ ነጥብ ለማስመዝገባችን ሙስናዓ ይነተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፤ እያደረገም ነው፡፡ ይህ ነገር በአሁኑ ወቅት የተሻለ መግባባት እና የህግ ማዕቀፍ ያስፈልገዋል፡፡ ከመግባባት አንፃር ከኮሪያ እና ታይዋን የምንማረው ይኖራል፡፡ እነዚህ ሀገሮች ፈጣን እድገት በሚያስመዘግቡበት ወቅት ሌቦች የተባሉት እንኳን ሲሰርቁ ለክተው ነበር፡፡ ለምሣሌ የትምህርት ቤት ግንባታ 1ዐዐ,ዐዐዐ ዶላር ቢፈጅ

መሀንዲሱ ዋጋውን 11ዐ,ዐዐዐ ዶላር ያደርገው እና 1ዐ,ዐዐዐ ዶላር ሌባው መሀንዲስ ከመንግሥት ካዝና ቢወስድም በት /ቤቱ መጠንና ጥራት እንዲሁም በሚጠናቀቅበት ጊዜ ግን አይደራደርም፡፡

የኤክስፖርት ምርት ደግሞ ምንም ሙስና አይፈፀምበትም፡፡ ምክንያቱም ኤክስፖርት የህልውና ጉዳይ መሆኑ መግባባት ስለተደረሰበት ነው፡፡ እኛ ግን የኤክስፖርት ቡና
እንሰርቃለን እንቀሽባለን፡፡ ቡና ለኢትዮጵያ ከኤክስፖርትም በላይ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያን ህዝብ በሙሉ እንደሙጫ የሚያስተሳስር ማህበራዊ ካፒታላችን ነው፡፡

ታዋቂው የአሜሪካ የፖለቲካ ሣይንስ ምሁር ሮበርት ፑትማን እንደሚለው የማህበሪዊ ካፒታል እየተስፋፋ መሄድ ለአንድ ሀገር ብሔራዊ ብልፅግናና የደሞክራሲ ማበብ በከፍተኛ ሁኔታ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ፑትማን እንደሚለው የማህበራዊ ካፒታል መሳሳት ደግሞ

የሀገርን እድገት ወደ ኋላ በመጎተት ብሎም በማቀጨጭ በህብረተሰቡ መካከል ያለውን መልካም መስተጋብርን ያላላል፡፡ ለዚህም በምሣሌነት የሚያነሣው በደቡባዊና
በሰሜነናዊ ኢጣሊያ ያለውን የእድገት ልዩነት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ በቡና ላይ የሚፈፀም ሙስና በአርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነት ላይ አሉታዊ ተጽአኖ በማሣደር የቡናችንን ቀጣይነት አጠያያቂ በማድረግ ማህበራዊካ ፒታላችንን የሚያላላ ሊሆን ይችላል፡፡ ቡና ከማህበራዊ ካፒታልነቱ በተጨማሪ የሀገራችን መለያ /ብራንድ/ ነው፡፡ ጀርመን ሲቪል ኢንጅነሪንግ፣ ፈረንሣይ ሲባል ሽቶ፣ ብራዚል ሲባል ደግሞ እግርኳስ፣ ኢትዮጵያ ሲባል ቡና ነው፡፡ ብራንድ ደግሞ አይሠረቅም፡፡ ለምሣሌ የብራዚል እግርኳስ ቡድን ለዋንጫ ቀርቦ ጉቦ በመቀበል ተሸነፈ ተብሎአል ተሰማም፡፡ የቡና ኤክስፖርትም ከዚህ አኳያ መታየት አለበት፡፡

ሲጠቃለል በሀገሪቱ ያለው ሙስና አፀያፊ መሆኑ ቀርቶ ዛሬ የሚሠርቅ ሰው ቢዝነስ ሠራ፤ ጀግና ተብሎ የሚወደስበት ጊዜ ላይ ተደርሷል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለሁላችንም የሚበቃ ሀብት አለን፤ ሁላችንም የምንዘርፈው ሀብት ግን የለንም፡፡

በፀሐፊው እምነት ሌቦች የሚሠርቁበት አንዱ ምክንያት የህግ ክፍተትን በማየት ነው፡፡ ለምሣሌ የሚያገኙት ጥቅም ከሚደርስባቸው ቅጣት የሚበልጥ ሲሆን ለስርቆት ይነሳሳሉ፡፡ ስለዚህ በላሉ ህጎች ምትክ የህግ ማሻሻያ ያስፈልጋል፡፡ ለምሣሌ የኤክስፖርት የቡና ሌብነት የሀገሪቱን አጠቃላይ ገፅታ የሚያበላሽ በመሆኑ እና በሀገሪቱ መለያ /ብራንድ/ የተደረገ ስርቆት በመሆኑ እንደ ሀገር ክህደት እና አገርን እንደመሸጥ ተቆጥሮ ለምን በሞት እንዲቀጡ የሚያደርግ ህግ አውጥተን አንተገብርም?

ከቻይና ትወራ (ንድፈ – ሃሳብ) ብቻ ሳይሆን ተግባርም ብንማርስ!

(ጸሃፊው አቶ ስንታየሁ ግርማ በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የሥነምግባር መከታተያ ዋና ክፍል ሀላፊ ናችው)

Related Post