አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

በሞቴ ስሙኝማ!!

በሞቴ ስሙኝማ!!
በሞቴ ስሙኝማ!!

በናፍቆት ዮሴፍ –

ቤቴ ትንሽ የሚያልቅ ነገር ነበራትና ግንበኞች ይሰሩ ነበር።ከሁለቱ አንዱ ከፖሊስ ጣቢያ ተደውሎለት ሊሄድ ሲነሳ ጓደኛው ምን ያህል ጊዜ ይወስድብሃል ብሎ ጠየቀው።”መመለሴንስ በምን አውቄው” ሲል መለሰ። ከዛ ለጓደኛው ምን ሆኖ ነው ከስራ ሰዓት ውጪ በፖሊስ የተጠራው ብዬ ጠየቅኩት።

ከአራት ዓመት በፊት ትንሽ ሞቅ ብሎት ይህ መከረኛ ልጅ ከፖሊስ ይጣላል። ፖሊሱ ልብሱን ጨምድዶ ሲይዘው ጓደኛው ያይና መጥቶ ፖሊሱን በቦክስ አቅምሶት ያመልጣል። ያንን ፖሊስ ሲማታ ያየው ሌላው ፖሊስ ጓደኛህ ፖሊስ ደብድቦ ተሰውሯል እሱን ካላመጣህ አስርሃለሁ እያለ እያስፈራራ እስካሁን ገንዘብ ይቀበለዋል።

ዛሬም ተደውሎለት በሄደ በ20 ደቂቃ ውስጥ ተመልሶ ወደቤቴ መጣና ከጓደኛው ጋር ስራውን ቀጠለ። ለምን ነበር ፖሊስ በዚህ ሰዓት የፈለገህ አልኩት። ከላይ ያለውን ታሪክ ከነገረኝ በሗላ “ብር አምጣ አለኝ 1000 (አንድ ሺህ ብር) ከኤቲኤም አውጥቼ ሰጥቼ መጣሁ ከዚህ በሗላ ብር ከጠየቀኝ የምሰጠው የለኝም ኑሮውም ከብዶኛል ወስዶ ይሰረኝና መንግስት ይቀልበኝ”ብሎ ሲማረር ብስጭቴን መቆጣጠር አልቻልኩም። እግዜር ያሳያችሁ በዚህ ኑሮ በአንድ የቀን ሰራተኛ ላይ ይሄ ጭካኔ አይሰቀጥጥም?ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍ😭😭😭😭😭

Related Post