አርእስተ ዜና
Mon. Jan 27th, 2025

ሥነ ምግባር ለምን ያስፈልጋል?

ስነ ምግባር ለሰው ልጅ ጤናማ አኗኗር ወሳኝ ነው፡፡ የድርጊት መርሃ ግብርናችነን ለመወሰን ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ያለ ሥነ ምግባር ወደ ምንፈልገው ግብ መድረስ አንችልም፡፡ ጥሩ ስነ ምግባር ከሌለን የሰው ልጅ ፍላጐቶች እና ግቦች ማለቂያ ስለሌላቸው ወደ ግቦች መድረስ አንችልም፡፡

ጥሩ ስነምግባር ኖሮን እንኳን አንዳ አንዴ ግባችንን ለማሳካት አዳጋች ያደርግብናል፡፡ ምክንያቱዳዊ እና ደረጃውን የጠበቀ ሥነ ምግባር ሲኖረን ግባችን እና ድርጊታችንን በአግባቡ ለማደራጀት ያስችለናል፡፡ መጥፎ ሥነምግባር ወደ ግባችን ለመድረስ የምናደርገውን ጥረት ያሰናከልብናል፡፡

ሰዎች ስለ ስነምግባር ያላቸው አስተያየት የተለያየ እና የሚገርሙ ናቸው፡፡ ብዙ ሰዎች ስነምግባርን ከስሜት ጋር ያያይዙታል፡፡ ይሁንና ሥነምግባር ማለት ስሜታችንን መከተል ማለት አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ስሜቱን ተከትሎ የሚያደርገው ድርጊት ትክክለኛ ላይሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ስነምግባርን ከሀይማኖት ጋር ሊያይዙት ይችላሉ፡፡ ይሁንና ሥነ ምግባር ሀይማኖተኞች ብቻ ሣይሆን ሀይማኖት የለሽችንም ይመለከታል፡፡ ስነምግባር ህግን ማክበርን ፤መከተል ጋር አንድ ዓይነት አድርጐ መውሰድ ትክክል አይደለም፡፡

ምንም እንኳን ህግ ብዙውን ጊዜ የህብረተሰቡን ሥነ ምግባር ተከትሎ ቢቀረፅም አንዳ አንድ ህጐች ከሥነ ምግባር ያፈነገጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሥነ ምግባር የድርጊትን ትክክለኛነት ለማረጋገጠ ስታንዳርድ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በሌላ አባባል የሥነ ምግባር ስታንዳርድ የአንድን ድርጊት ትክክለኛነት ለመመዘን ያስችላል፡፡ ድርጅቶች የብዙ ባለድርሻ አካላትን ፍላጐትን ለማርካት የተቋቋሙ ናቸው፡፡

ስለዚህ የየትኛው ባለድርሻ አካል ግብ ትክክል እንደሆነ እና ድርጅቱ የእነሱን ግብ ለማሣካት የትኛውን ዘዴ መጠቀም እንዳለበት ማህበራዊ ሀላፊነትን ግምት ማስገባት ይገባል፡፡ ስለዚህ ድርጅቶች ለውኔያቸው የሥነ ምግባር ስታንዳርድ መሠረት ነው፡፡ ህብረተቡ ከዬትኛውም ምክንያታዊ ቢሮክራሲ ፍትሃዊ– እና ትከክለኛ ወሣኔ ይጠብቃል፡፡

ሥነ ምግባር ምንድ ነው?
በዋነኝነት ሥነ ምግባር ማለት ሁለት ነገሮች ይይዛል፡፡ የመጀመሪያው በአግባቡ መሠረት ያለው እና የተረጋገጠ ትክክለኛውን ከስህተት፣ ለመለዬት የሚያስችል ህብረተሰቡን የሚ-ተገብረዉ..

ብዙን ጊዜ በመብቶች፣ በግዴታዎች፣ ለህብረተሰቡ በሚሰጠው ጠቀሜታዎች፣ ፍትሀዊነት የያዘ ነው፡፡ ሥነ ምግባር ለምሣሌ ከአስገድዶ መድፈር እንድንርቅ፣ ከመስረቅ፣ ከመግደል፣ ከማመነጫጨቅ፣ ከማጭበርበር ወዘተ እንድንርቅ ግዴታዎችን ያስቀምጣል፡፡ ሥነ ምግባር ታማኝ፣ ቅን፣ ረህሩህ እንድንሆን ስታንዳርድ ያስቀምጣል፡፡ ሥነ ምግባራዊ ስታንደርድ ከመብቶች ጋር ለምሣሌ በህይወት የመኖር ፤ከጉዳት የመጠበቅ፣ የግል ጉዳዮች መጠበቅ የሚያስችል ስታንዳርድ ያስቀምጣለ፡፡ አነዚህ ስታንዳርዶች በቂ እና አስተማማኝ ምክንያት ደግሞ ብዙውን ጊዜ ቀጣየነት ያላቸው እና በአግባቡ የተመሠረቱ ናቸው፡፡

ሁለተኛው የሥነ ምግባር ትርጉም የስነ ምግባር ስታንደርድን ማጥናት እና ማበልፀግ ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጠው ስሜቶች ህጐች እና የማህበረሰቡ ኑሮዎች አንዳንዴ ከሥነ ምግባር ያፈነገጡ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በተደጎጋማ የተቀመጡ ስታንዳርዶች ምክንያታዊ እና ጥልቅ መሠረቶች ያላቸው መሆኑን በተከታታይ መመዘን ይጠይቃል፡፡ ስነምግባር በተጨማሪ ስለ ሞራላዊ እምነቶች /moral belief/ ሞራላዊ ፀባዮች /moral conduct/ በተደጋጋሚ ለማጥፋት ጥረት የሚያደርገው ነው፡፡ የምንገነባው ተቋም ስታንደርድና ምን ያህል ምክንያታዊ እና መሠረቶች ያላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ሥነ ምግባር ይረደናል፡፡

ሥነ ምግባር /የሞራል ፍልስፍና/ ስለሞራሊቲ የሚያጠና የፍልስፍና ጥናት ነው፡፡ ሞራሊቲ ስለ ትከክለኛ /አሠራር/ ጥሩ እና መጥፎ ያለን እምነት /belief/ ነው፡፡ ሞራልቲ ምከንያታዊ ፍርድ /judge/ ፣ እሴቶችን፣ ህጐችን፣ -ትወራዉችን፤መርሆዎችን ያጠቃልላል፡፡ ሞራሊቲ ድርጊታችንን ይመራል፣ እሴቶቻችንን ይገልጻል፣ የሰው ልጅ ለመሆናችን ምክንያት ይሰጠናል፡፡ ሥነ ምግባር ደግሞ የፍስፍና አካል ሆኖ ስለሞራሊቲ ያሉንን ጥያቄዎች ለመመለስ ያስችለናል፡፡ መጥፎም /ጥሩ/ ትክክለኛ ስህተት፣ ፍትሀውነት አና በጐነት /—virtue-/ የሚባሉት ፅንስ ሀሣቦችን ያጠናል፡፡

“የስነ ምግበር ባህሪያት”
በጥሩም ሆነ በመጥፎ እንደ ሥነምግባር ተጽእኖ ያለው ጉዳይ የለም፡፡ ተጽእኖውም በሀገሪቱ በሰው ልጅም ሆነ በሀገር ላይ ከፍተኛ ነው፡፡
ያለጥሩ ሥነ ምግባር ያደገ /የበለፀገ/ ሀገር የለም፡፡ ለምሣሌ የአውሮፖውያንም ሆነ የምሥራቅ ኤስያ ሀገራት ብልፅግና ካለጥሩ ሥነ ምግባር አይታሰብም፡፡

በሌላ በኩል መጥፎ ሥነ ምግባር በታሪክ ከፍተኛ ጉደይ አድርሰዋል፡፡ ለምሣሌ የ1ኛው እና የ2ኛው የአለም ጦርነቶች፣ የሩዋንዳ የዘር ፍጆታ፣ የሌማን ብሪዘርስ ባንኮች ወለሠም ወዘተ መጥቀስ ይቻላል፡፡

ስነ ምግባር “ተሻጋሪ” ባህሪያት አሉት
ስነ ምግባር የሰው ልጅ ሥልጣኔን ባህል ርኦተ አለም እና ሀይማኖትን ተሻጋሪ ነው፡፡
ሥነ ምግባር የሁሉም ሀይማኖቶች ምሶሶ ነው፡፡

“ሀይማኖት ያለ ሥነምግባር የሰናጣን፣ ሥነምግባር ያለ ሀይማኖት የበጐ አድራጐት ሥራ ነው” መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ሁሉም ሀይማኖቶች የስነ ምግበር ኮድ አላቸው፡፡ “ወርቃማ ህግ” አላቸው የኘብሊክ ሰርቪስ እና ስነምግባር “ቁርኝት” የሁሉም ግንኙቶችን በተመለከተ የኘብሊክ ሠርቪስ ያለ ሥነ ምግባር በአግባቡ አገልግሎቱ ሊሰጥ አይችልም፡፡

በፅንሱ ሀሣብ ደረጃ የመንግሥት አገልግሎቶች እና ሥነ ምግባር ሊለያዩ አይችሉም፡፡ በተፈጥሮው የመንግሥት አገልግሎት የሥነ ምግባር ኢንተርኘራይዝ ነው፡፡
የመንግሥት ሠራተኞች የህዝብ ጥቅም ጠባቂዎች ወይንም አሣዳጊዎች ናቸው፡፡ ሰቭል ሠርቪስ የልማት እና ጥሩ አፈፃፀም ዋነኛ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
እነዚህ በሙሉ ያለ ሥነ ምግባር ሊፈፀሙ አይችሉም፡፡

በአለም ላይ በአንድ ድምፅ ሥነ ምግባር ከሁሉም በላይ መሆኑን ስምምነት አለ
በሰው ልጅም ሆነ በሀገር ላይ እንደ ሥነ ምግባር በማንም ሆነ በጥሩ ተፅዕኖ ያለው ጉዳይ ያሳየ ያለጥሩ ሥነ ምግባር የበለፀገ ሀገር የለም፡፡ ማንም ሥነምግባር ሁለት አውዳዊ የአለም ጦርነቶችን አስከትሏል፡፡
ምንጭ፡ሺቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ

Related Post