አርእስተ ዜና
Wed. Dec 25th, 2024

ሌሎችም ከዚህ መማር አለባቸው

ሌሎችም ከዚህ መማር አለባቸው
ሌሎችም ከዚህ መማር አለባቸው

በተሁዉቦ በማርያም ንጉሴ – ከትላንት በስትያ ሁለት ዓመት ሙሉ ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቅባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች በሦስትና በሳምንት ልዩነት የሐራጅ ጨረታ ወጥቶባቸው ነበር።

ሰው ለአንድ ቪትዝ የተነዳ መኪና አንድ ሚሊየን ብርና ለሌላውም ቢሆን ከዛ በላይ ጨረታው ላይ አቅርበዋል።
ዋጋው ከከተማ መኪና መሸጫ ጋር ሲነፃፀር አይቀራረብም ያበደ ነበር።
የሆነው ሆኖ……..

በየሁኔታው ሐገር ጥለው ተሰደው የእናት አባት መጦሪያ ንብረት አስይዘው ወደ ሥራ የገቡ የሐገር ልጆች በዚሁ ጉዳይ አልቅሰዋል።
የሚያጭበረብሩ እንዳሉ ሁሉ በትክክለኛው መንገድ ደግሞ ሰነድ ያላቸው አስመጭዎች አብረው ተጨፍልቀዋል።
ይህ በፍፁም ትክክል አይደለም።

ሰሞኑን ግን ነገሩ የመኖርና ጎዳና ላይ የመውደቅ ጉዳይ ስለሆነ ትክክለኛ ሰነድ አለን ችግሩ የኛ አይደለም ያሉት የሐገር ልጆች የገንዘብ ሚንስትር ድኤታን ቢሮ ደጅ ጠንተዋል።

ምንስትር ድኤታ እዮብ ተካልኝ (phd) በብርቱ አድምጠዋቸዋል።
ልጆቹ ከፊቱ ቆመው ስቅስቅ ብለው ማልቀሳቸውን ሰምተናል።

ጉዳዩ ምን ይሁን ምንም ምንስትር ድኤታው በወንበር ብቻ ሳይሆን በሁሉም መዓዘን አድምጠዋል ተብሏል።
ነገሩን ለመመልከትም ትዕግስትና የሐገር ልጆችን ችግር መስማታቸውን አውቀናል።

ይህ ለሌላውም ቢሆን ተስፋ የሚሰጥና አስተማሪ ነው ብለን እናምናለን።
ዛሬ ለሐገር የሚጠቅም ጉዳይ እንኳ ይዛችሁ እንኳን አይደለም በሚንስተር ደረጃ አንድ የክ/ ከተማ ኃላፊ ለማግኘት ፀሐፊዋ አታደርሳችሁም በቢሮክራሲ ቀድማችሁ ነው አናታችሁ የሚፈርሰው።

ሌሎችም ከዚህ መማር አለባቸው ብለን እናምናለን።
በነገራችን ላይ ከዚ ቀደም የተወሰኑ ተሽከርካሪዎቹ ከአስመጭዎቹ እውቅና ውጭ መሸጣቸውንና አራት ቁጥር ለጥፈው በከተማው ሲዘዋወሩ ታይተዋል።

The best result would come from everyone in the groups 👥 doing what 😦 is best for himself and the group 👥.
By z way we are not 💺 in sail shape design, and the lavish suite, expensive five ⭐ hotel or Looby it is his office.
Let’s stand with 🇪🇹

Related Post