አርእስተ ዜና
Sat. Nov 23rd, 2024

የኢትዮጵያ ቀን በበርን ከተማ ስዊዘርላንድ ተከበረ

የኢትዮጵያ ቀን በበርን ከተማ ስዊዘርላንድ ተከበረ
የኢትዮጵያ ቀን በበርን ከተማ ስዊዘርላንድ ተከበረ

በጄኔቫ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕከተኛና ባለ ሙሉሥልጣን አምባሳደር አምባሳደር ዘነበ ከበደ የሕዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር ዉሃ ሙሌት መጠናቀቅ የጸረ ኢትዮጵያ ቡድን አባላትን ተስፋ ያስቆረጠ፤ በአገራችን ታሪክ ውስጥ አዲስ ምእራፍ የከፈተ ነው ብለዋል።

ክቡር አምባሳደር ይህን ያሉት ‘የኢትዮጵያ ቀን’ የስዊዘርላናድ በርን ከተማ ሲከበር ባስተላለፉት መልዕክት ነው። ሦስተኛው ዙር ዉሃ ሙሌት መጠናቀቅ እና ሁለተኛው ተርባይን ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የቀጣይ ተስፋችንን ያመላከተ እና በግድቡ ግንባታ የተሳተፉ መላው ኢትዮጵያውያንን ያስደሰተ ነው ያሉት ክቡር አምባሳደር ዘነበ፤

የግድቡ ቀሪ ግንባታ እንዲጠናቀቅ ቦንድ በመግዛት እና ስጦታ በመለገስ የዳያስፖራው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ክቡር አምባሳደር በአጽንኦት አሳስበዋል። ዳያስፖራው በውጭ ያፈራውን ሀብት እና ያካበተውን እውቀት በአገራችን እድገትና ልማት ላይ በማዋል፤ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በመገንባት እና ባጠቃላይ ለአገሩ ዘብ በመቆም እያደረገ ያለውን ከፍተኛ እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል አምባሳደር ዘነበ ጥሪ አድርገዋል።

ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤቱም ከዳያስፖራው ጋር የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው ስራ ለመስራት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል:: የኢትዮጵያን በጎ ገጽታ በስዊዘርላንድ እና በመላው ዓለም በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ ለሆኑ በስዊዘርላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ግለሰቦች እና ማህበራት ከአዘጋጆቹ የዕውቅና ሰርቲፊኬት ተበርክቶላቸዋል::

Related Post